ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ስንቅ ነው

AMN- ጳጉሜን 3/2018 ዓ.ም

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያዊያን የፅናት ማሳያ ብቻ ሳይሆን የ”ይቻላል” መንፈስን የፈጠረና ለሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መነሳሳት ስንቅ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኒእመተላህ ከበደ ከኤ ኤም ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ግድቡ በብዙ ፈተናዎች አልፎ የአይቻልምን ግርዶሽ የገፈፈ የፅናት ተምሳሌት ነው፡፡

በፅናት የቆመ ሕዝብና መንግሥት የማያልፈው ችግር እንደሌለ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስኪያጇ፣ ኢትዮጵያዊያን የፅናት ቀንን ሲያስቡ በየተሰማሩበት የስራ መስክ የሚጠበቅባቸውን ሊያበረክቱ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የተባበረ ሕዝብና አቅሙን ያደራጀ መንግሥት ረጅሙን የስኬት ጎዳና መጓዝ እንደሚችል የጠቆሙት ዋና ሥራ አስኪያጇ፤ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መነሳሳት ስንቅ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

በደሴ ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review