AMN- ጳጉሜን 05/ 2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ከመስከረም 2019 ዓ.ም ጀምሮ 1ሺ ሴቶች ወደ ስልጠና እንደሚገቡ የነገዋ ሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀግያ ማዕከል ገለጸ፡፡
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ሄርጳሳ ጫላ(ዶ/ር) እየተከበረ ያለውን የነገ ቀንን አስመልክቶ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት ፣ ከሁለት አመት በፊት ውስብስብ ችግር ውስጥ የነበሩ ሴቶች የተሻለ ህይወት እንዲኖራቸው ለማስቻል በተጀመረው ፕሮጀክት ከ3ሺ 258 በላይ ሴቶች ተጠቀሚ ሆነዋል፡፡

በዚህም ሰሴቶቹን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ወደ ስራ በማስገባት ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል ብለዋል።
ሴቶችን ማገዝና ማብቃት ሀገርንና ህዝብን ማብቃት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የነገ ቀንን ስናስብ ነገ በተሻለች ሀገር ለመኖር የሚያስችል ምቹ መደላድል ለመፍጠር በተጀመረው ስራ ሁሉም መሳተፍ ይገባል ብለዋል።

ከመስከረም 2019 ዓ.ም ጀምሮ 1ሺ ሴቶች ወደ ስልጠና ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለጹት፡፡
ትናንት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ የነበሩ ዛሬ ግን ነጋቸውን ብሩህ ለማድረግ ተስፋ በሰነቁ ሴቶች የተሞላው የነገዋ ሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀግያ ማዕከል ለብዙ እንስቶች እፎይታ ማስገኘቱን የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ሄርጳሳ ጫላ(ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
በደሴ ብርሃኑ