ኢትዮጵያ የፋይናንስ ተደራሽነት እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ያስፈልጓታል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ኢትዮጵያ የፋይናንስ ተደራሽነት እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ያስፈልጓታል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- መስከረም 3/2019 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የፋይናንስ ተደራሽነት እና ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ያስፈልጓታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ አሁን ላይ ቴክኖሎጂ በፍጥነት እያደገ ነው ብለዋል፡፡

ፍትሃዊ የሆነ ዓለም አቀፍ ስርዓትን መፍጠር እና የኢኮኖሚ እድሎችን ማስፋትም እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አክለውም፤ የፋይናንስ ተደራሽነት ንግድን ይደግፋል፣ ኢንቨስትመንትን ያበረታታል ብለዋል፡፡

በዚህም ግዙፍ ኢኮኖሚና ብዙ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ የባህር በርና አስተማማኝ ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች ያስፈልጓታል ነው ያሉት፡፡ የባህር በር ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እጅግ አስፈላጊና ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት እየሰራች ነው፤ ጥያቄዋ በጋራ ተጠቃሚነትና የጋራ እድገት የተመሰረተ ነው፡፡ ብሪክስ ለአባል ሀገራቱ እድገትና የወደፊት እጣ ፋንታ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባልም ብለዋል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review