300 የሕገ ወጡ ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጡ

You are currently viewing 300 የሕገ ወጡ ህወሓት ቡድን ታጣቂዎች ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጡ

AMN – መስከረም 8/ 2019

የሰላም ጠሉ ህወሓት ለጦርነት የሚያደርገውን ዝግጅት በመጥላትና ከቡድኑ ጋር ሆነው አለመዋጋትን በመምረጥ ወደ 300 የሚጠጉ የህወሓት ታጣቂዎች በተከዜ በኩል ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ሰሜን ምዕራብ ዕዝ እጃቸውን ሰጥተዋል።

በምዕራብ ግንባር ተከዜ አቅጣጫ ልዩ ቦታው በተከዜ ድልድይ ግራና ቀኝ አቅጣጫ ለዕዙ ሠራዊት እጅ የሠጡ የህወሓት ታጣቂዎች የኢትዮጵያና የትግራይ ህዝብ ጠላት ሆኖ የትግራይን ህዝብ ሲጨፈጭፍ ከነበረው ሻዕቢያ ጋር ፅምዶ በሚል እሳቤ የፈጠሩት ጥምረት ለትግራይ ህዝብ የማይጠቅምና የሚጎዳ መሆኑን በመገንዘብ በቀጠናው ከሚገኘው መከላከያ ሠራዊት ጋር ቀደም ብለው በመሠረቱት ግንኙነት በመነጋገር እና መንገድ በማመቻቸት እጅ መሥጠት እንደቻሉ ተናግረዋል።

የትግራይ ህዝብ ጥያቄ የሚፈታው በጠብመንጃ ሳይሆን በመነጋገር እና በመግባባት ነው የሚል እምነት ይዘው ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሠራዊት እጅ የሠጡት የህወሃት ታጣቂዎች ከሁለት መቶ ሰማንያ በላይ የነፍሰ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ በርካታ የተለያዩ ዓይነት ተተኳሾች፣ የጦር ሜዳ መነፅርና ልዩ ልዩ ዶክመንቶች ይዘው መግባታቸውንም ዕዙ አስታውቋል።

ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን ሠላማዊውን የትግራይ ህዝብ ወጣት በማፈስ ወደ ጦርነት ለመማገድ የሚሠሩ ዘራፊ እና ወርቅ አውጪ የህወሃት አመራሮችን ፍላጎት በመቃወም እጅ የሠጡት የሕገ ወጡ ህወሃት ታጣቂዎች አሁንም ቢሆን አለመግባባቱ ሊፈታ የሚችለው በጥቂት ጨቋኝ የህወሃት አመራሮች ፍላጎት ሳይሆን በመነጋገር ብቻ ነው የሚል ሙሉ እምነት ይዘው እጅ መሥጠታቸውንም ተናግረዋል።

እጅ ከሰጡ የህወሃት ታጣቂዎች መካከል ከክፍለጦር አዛዥ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሻለቃና የሻምበል አመራሮች ይገኙበታል ያለው ዕዙ ይህ የሚያመላክተው ታጣቂው ሃይል ሳይፈልግ በህወሃት ሥርዓት አገዛዝ አሥገዳጅነት የሚዋጋ ኃይል ስለመሆኑ እንደሆነም ገልጿል።

ሕገ ወጡ ህወሃት ከጦርነት አዙሪት የመውጣት ፍላጎት የሌለው ፅምዶ በሚል አካሃድ ህዝቡን አሁንም ወደ ከፋ ችግር ውስጥ ለመክተት የሚጥር፤ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ለሠላም የማይመች፤ የቀረበለትን የሠላም አማራጭ የማይቀበል በትግራይ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሥለመሆኑም እጅ የሠጡ ታጣቂዎች ተናግረዋል።

አሁን ላይ የህወሃትን የአገዛዝ ሥርዓት በመጥላትና ሠላምን በመምረጥ እጅ ለመስጠት የሚጠባበቁ በርካታ የትግራይ ወጣቶች አሉ ያሉት ታጣቂዎቹ የትግራይን ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለመነጠልና ሠላም ለማሳጣት ህወሃት ወጣቱን እያስገደደ ሳይፈልግ ለጦርነት እያዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ተገዶ የገባው የትግራይ ወጣትም ይህን አውቆ እና ተረድቶ ጊዜና ሁኔታው ሲመቻችለት እጅ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ታጣቂዎቹ መግለጻቸውን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review