ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለኢሬቻ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለኢሬቻ በዓል ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

እንኳን ለታላቁ የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ኢሬቻ የኦሮሞ ማኅበረሰብ የክረምቱን ዝናብና ፈተና አልፎ፣ ተፈጥሮ በአረንጓዴ ውበቷና በአደይ አበባ ተሸምና፣ የብራ ወቅት ሲበሰር ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት ውብ የምስጋና በዓል ነው።

ኢሬቻ ያለፈውን በምስጋና የሚያስታውስ፣ የአሁኑን በሰላም የሚያከብር፣ መጪውንም በተስፋ የሚቀበል የአብሮነት መገለጫ ነው። ሕዝቡ ለተቀበለው በረከት ምስጋና ያቀርባል፤ ለአዲሱ ዘመንም ሰላም፣ በረከትና ብልጽግና ይሰፍን ዘንድ ጸሎት ያቀርባል።

ኢትዮጵያ እንደ ኢሬቻ ባሉ የጋራ ዕሴቶቿ ላይ ተመሥርታ፣ ብዝኃነቷን ወደ ኅብረት፣ ኅብረቷን ወደ ዐቅም፣ ዐቅሟን ወደ ልማት፣ ልማቷንም ወደ የጋራ ሥልጣኔ ለመቀየር የምትጓዝበትን መንገድ እያጠናከረች ነው።

ኢሬቻ የሚያስተምረን ታላቅ ትምህርትም ይህ ነው፤ በአንድነት ስንቆም ዐቅማችን ይጨምራል፤ በመተሳሰብ ስንጓዝ የሩቅ ሕልማችንን ወደ ቅርብ እውነታ እናመጣለን፤ በጋራ ስንሠራ የጋራ ተስፋችንን ወደ ተጨባጭ ፍሬ እንቀይራለን።

በዓሎቻችን መነሻቸው አንድ አካባቢ ነው። በሂደት ግን የሁላችንም ሆነዋል። እኛም ለዓለም አበርክተናቸዋል። ያከብሩናል፤ ያስተሣሥሩናል፤ ያበለጽጉናል።

ኢሬቻ የሰላማችን መሠረት፣ የአብሮነታችን ጥንካሬና የጋራ ነጋችን ይበልጥ የሚያበራበት በዓል ይሁን!

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review