ኢትዮጵያ በሰብል ምርት የ1 ቢሊዮን ኩንታል ጭማሪ በማስመዝገብ ታሪካዊ እምርታ አሳይታለች – ፕሬዘዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

AMN- መስከረም 26/2019 ዓ.ም

በኢትዮጵያ በ2011 ዓ.ም ከነበረው 335 ሚሊዮን ኩንታል ዓመታዊ የሰብል ምርት በ2018 ዓ.ም ወደ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ማደጉንና የ1 ቢሊዮን ኩንታል ጭማሪ መመዝገቡን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ።

የሕዝብ ተወካዮች እና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባቸውን አካሂደዋል።

ፕሬዚዳንቱ ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ባደረጉት ንግግር ፣ ይህ ታላቅ የምርት እምርታ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ልዑላዊነት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር ታላቅ ስኬት ነው ብለዋል።

ሀገሪቱ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ 11 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ ማስመዝገቧን ፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን፣ የአምራች ኢንዱስትሪ እድገት 15 ነጥብ 8 በመቶ ከፍ ማለቱን፣ የብድር አቅርቦት ወደ 1 ነጥብ 3 ትሪሊዮን ብር ማደጉን እና ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ገቢ 1 ትሪሊዮን 980 ቢሊዮን ብር መድረሱን ጠቅሰዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህ ውጤት በበርካታ አካላት ጥረትና በሕዝቡ ታታሪነት የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

በታደሰ ሽፈራው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review