የህገወጥ ቡድኑ ገመና ተጋለጠ!

AMN መስከረም 27/2019 ዓ.ም

ህገ ወጡ የህወሃት ቡድን ላለፉት አርባና ሃምሳ አመታት የሻዕቢያንና የግብጽን የጥፋት ተልዕኮ በግንባር ቀደምትነት ሲያስፈጽም ኖሯል።

ኢትዮጵያን የባህር በር ከማሳጣት: የሰሜን ዕዝን በግፍ ከመጨፍጨፍ እና ከሻዕቢያና ከግብጽ ጎን ተሰልፎ እናት ሃገሩን ከመዉጋት ጀምሮ በርካታ የሃገር ክህደት ተግባራትን ፈጽሟል።

በትግራይ ክልል ዘላቂ ሠላምና ልማት እንዳይሰፍን: ህዝቡ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ዉጥቶ የልማት ተጠቃሚ እንዳይሆን በተደጋጋሚ እንቅፋት ሆኗል።

በተቃራኒዉ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ ልማትና ነጻነት የቆምኩት ብቸኛዉ ታጋይ እኔ ብቻ ነኝ በማለት ህዝቡን ለረጅም አመታት ለማታለል ሞክራል።

የህወሃትን ፖለቲካ በቅርበት የሚያዉቁ አንዳንድ ምሁራንና የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚናገሩት ከሆነ የጽንፈኛ ቡድኑ አጠቃላይ የፖለቲካ ህይወት የተመሠረተዉ በሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች ላይ ነዉ።

ቡድኑ ሆን ተብለዉ በሚፈበረኩ ሴራዎች: በሚቀናበሩ ሃሰተኛ መረጃዎችና ክሶች ህዝቡን ብቻ ሳይሆን የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ጭምር ግራ እስከማጋባትና ማታለል ደርሷል።

ጽንፈኛዉ ቡድን እስከ ዛሬ ድረስ በህይወት ሊቆይ የቻለዉም በትክክለኛ የፖለቲካ አላማ፤ በህዝብ ዘንድ ባለዉ ተቀባይነት: በታጠቀዉ የጦር መሳሪያና አለም ከጎኑ ስለቆመ ሳይሆን በሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች ብቻ መሆኑን የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

ዛሬ ላይ ግን ቡድኑ ለዉጭ ሃይሎች ከመላላክ ዉጪ ምንም አይነት የፖለቲካ አላማ የሌለዉ: ህዝባዊ ተቀባይነቱን ያጣ: በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ የተወገዘ እና ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ጋር የመገዳደር ሥነ ልቦናና ብቃት የሌለዉ ተራ የሽፍቶች ስብስብ መሆኑ በተግባር ተጋልጧል።

ሻዕቢያና ግብጽ ህገወጥ ቡድኑ ኢትዮጵያን እንዲያቆስልለት በዉስጥ ባንዳነት ከመጠቀም ዉጪ ከየትኛዉም ጥቃትና እርምጃ መከላከልና ማዳን እንደማይችሉም በተግባር ተረጋግጧል።

ለረጅም አመታት የትግራይን ህዝብ ሲያሰቃይ: ለልማት የተመደበን በጀት ሲዘርፍ: የክልሉን የወርቅ ሃብት ወደ አስመራ ሲያሸሽ: የሚቃወሙትን ሲያስር: ሲገድል: ወጣቶችን ለጦርነት ሲያሰልፍና ሲያፈናቅል የነበረን ሃይል ዛሬ ማንም ከሽሽት ሊታደገዉ አልቻለም።

ህገወጡ ቡድኑ በኤርትራ ምድር ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ የትግራይ ወጣቶችን አጥብቆ የሚፈልገዉ ለጦርነት ብቻ ነበር። ዛሬ ላይ ግን ሁሉም ትግራዋይ ጦርነት በቃኝ ብሎ ከጀግናዉ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ተሠልፏል።

ከጦርነትና ከግጭት ጋር ተወልዶ አብሮ ያረጀዉ ህገወጥ ቡድኑ ጽምዶ የሚባል ጥምረት ፈጥሮ ኢትዮጵያን ለመዉጋት ተዘጋጅቻለሁ ቢልም ጥምረቱ ከጎኑ ሊቆም አልቻለም፡፡

ከስህተቱ መማር የማይችለዉ፤ በንግግርና በምክክር የማያምነዉ እና ጦርነትን ብቸኛ መተማመኛዉ ያደረገዉ ጽንፈኛዉ ህወሃት በለኮሰዉ እሳት ራሱ እየተቃጠለ፤ ገመናዉም እየተጋለጠ ይገኛል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review