የነጻነት አርማ – የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ

AMN- ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ የአንድነት፣ የሉዓላዊነት እና የነጻነት ህያው ምልክት ነው።

የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ህብረ-ቀለማት ህዝቦች በጋራ የመኖር፣ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት በጋራ የመጠበቅ ጽኑ ፍላጎትንም የሚገልጽ ነው።

ኢትዮጵያ በታሪኳ በቅኝ ያልተገዛች፣ የነጻነትና የጽናት ምልክት ሆና በዓለም ብሎም በአፍሪካ በተምሳሌትነት ትጠቀሳለች።

የጥንት አባቶች ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው የጠበቋት ኢትዮጵያ የሠንደቅ ዓላማዋ ቀለማት የብዙ አፍሪካ ሀገራት የነጻነት አርማና የፓን-አፍሪካኒዝም ምልክት ለመሆን በቅተዋል።

ይህም ኢትዮጰያ ነጻነቷ ለራሷ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝብ የተስፋ ብርሃን እና የነጻነት ችቦ እንደነሆነ በሰፊው ያሳያል።

ሀገራዊ ክብር በህዝቦች አንድነት፣ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት እንዲሁም በላቀ ታሪካዊ እሴቶች ላይ ይገነባል።

በዲፕሎማሲ፣ በስፖርት፣ በኪነ-ጥበብ እና በሌሎች መድረኮች የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ኩራት ይሰማዋል።

የህዝቦችን ብዝሃነት፣ ታሪክና ባህል አቅፎ የሚይዝ የጋራ ጥላ የሆነውን ሠንደቅ ዓላማ የሰላም፣ የፍቅርና የጋራ እድገት ማሰሪያ አድርጎ በመጠቀም የሀገርን ሉዓላዊነትና ክብር ዘላቂ ማድረግ ይገባል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review