ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ ትውልድ ተሻጋሪ የሥልጣኔ ጉዞን ለመጀመር የተቀረጸ ፍኖተ ካርታ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ ትውልድ ተሻጋሪ የሥልጣኔ ጉዞን ለመጀመር የተቀረጸ ፍኖተ ካርታ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ኅዳር 17/2019 ዓ.ም

ታላቁ የመደመር ስትራቴጂ ከመንግሥታት ዕድሜና ከትውልድ የሚሻገር ዘላቂ የሥልጣኔ ጉዞን እውን ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ፍኖተ ካርታ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።

ስትራቴጂው ሲቀረጽ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገች ብትሆንም ዜጎቿ በድህነት ውስጥ የሚገኙበትን ነባራዊ ሁኔታ እንዴት መቀየር ይቻላል የሚለው ጉዳይ በጥልቀት መጠናቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል።

ከዚህ በመነሳትም ሀገሪቱ የት መድረስ እንዳለባት የሚያመላክቱ ግቦችን ከማስቀመጥ ባለፈ፤ ግቦቹን ለማሳካት የሚያስችሉ አቅሞችን፣ ግልጽ የጉዞ አቅጣጫዎችን እንዲሁም ልማት ከተረጋገጠ በኋላ የሚመጣውን ዕድገት በአግባቡ ማስተዳደር የሚቻልበትን ስልት አካትቶ መያዙን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል።

እነዚህን ግቦች እውን ለማድረግ ሀገር የሚገነባባቸው 15 ሞዴሎች መቀመጣቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልፀዋል፡፡

የሥልጣኔ ግንባታው ዋነኛ ዓላማ ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ጠንካራ መሠረት መጣል መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የአሁኑ ትውልድ ሀገር የመገንባት ታሪካዊ ኃላፊነት የተጣለበት ገንቢ ትውልድ መሆኑን ገልጸዋል።

ጉዳዩን በምሳሌ ሲያስረዱም፤ «የልጅ ልጆቻችን መሠረቱን ይረግጣሉ፣ ልጆቻችን ደግሞ ምሰሶውን ይይዛሉ፤ የእኔና የእናንተ ሥራ እየገነባን ጣሪያ ላይ መቀመጥ ነው» ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሀገር ለመገንባት መታደል መልካም ቢሆንም፣ የተገነባውን ሀገርና ሥልጣኔ ለቀጣዩ ትውልድ ማሸጋገር ግን ከፍተኛ ጥበብን የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review