የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አዲስ አበባ ገቡ

You are currently viewing የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አዲስ አበባ ገቡ

AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም

የአልጄሪያ ብሔራዊ ነፃነት ፓርቲ ዋና ፀሐፊ ፕሮፌሰር አብደልከሪም ቤን መባረክ የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመታደም አዲስ አበባ ገብተዋል።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሐሳብ ከጥር 23 እስከ 25 በአዲስ አበባ ያካሂዳል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review