ቡርኖ ፈርናንዴዝ የአል ሂላልን ጥያቄ ውድቅ ማድረግ አልቻለም

You are currently viewing ቡርኖ ፈርናንዴዝ የአል ሂላልን ጥያቄ ውድቅ ማድረግ አልቻለም

AMN-ግንቦት 22/2017 ዓ.ም

የማንችስተር ዩናይትዱ አማካይ ቡርኖ ፈርናንዴዝ የሰሞኑ መነጋገሪያ ሆኗል።

ፖርቱጋላዊው ተጫዋች ከሳውዲው ክለብ አል ሂላል ለቀረበለት ምራቅ የሚያስውጥ ገንዘብ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።

ዘአትሌቲክ እንዳወጣው ዘገባ ግን አሁን ላይ ስለዝውውሩ ማሰብ ጀምሯል። ወኪሉም ወደ ሳውዲ አቅንቶ ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛል።

የ30 ዓመቱ ተጫዋች የውድድር ዓመቱ መጨረሻ አስቶንቪላን ካሸነፉ በኋላ “ህልሙን እውን ማድረግ የቻለ ሰው ነኝ። ከአለማችን ምርጥ ክለቦች በአንዱ እጫወታለሁ ፤ በአለማችን ምርጡ ሊግ ላይ እሳተፋለሁ። ከዚህ በላይ ምን እፈልጋለሁ?” ብሎ ነበር።

ቡርኖ ይህን ቢልም ማንችስተር ዩናይትድን የመልቀቁ ነገር እውን ሊሆን ይችላል። ትልቁ ምክንያት ገንዘብ ነው።

አል ሂላል ለቡርኖ በአመት የተጣራ 25 ሚሊየን ዩሮ ለመክፈል ዝግጁ ነው። የአራት ዓመት ውልም ተዘጋጅቶለታል። ለዩናይትድም እስከ 100 ሚሊየን ዩሮ የመክፈል አቅም እንዳላቸው አሳውቀዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ 30 ዓመት ለሞላው ተጫዋች የቀረበለትን የዝውውር ገንዘብ ወድቅ የማድረግ አቅም ላይ አይገኝም።

የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ አጥቶ ገቢው የበለጠ የቀነሰበት ዩናይትድ ውሳኔው በትልቁ ይጠበቃል።

ህልሜን እየኖርኩ ነው ያለው ቡርኖ ፈርናንዴዝ ውሳኔስ ምን ይሆናል? በቀጣይ ቀናት የሚሆነውን ለማየት ያጓጓል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review