ለኢትዮጵያ የባህር በር ጉዳይ የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን የህልውናዋ ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተለያየ ጊዜ በአንክሮ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመላው ኢትዮጵያ ከተውጣጡ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ እንደ ሃገር ያለን ፅኑ አቋም የባህር በር የፖለቲካ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጥያቄ መሆኑ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የኢትዮጵያ የሁልጊዜም ፍላጎት ከጎረቤቶቿ ጋር በጋራ መልማት መሆኑንም በውይይቱ አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር እና ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ያላት ሃገር መሆኗን የገቀሰት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላም እና ልማት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ጉዳዮች እንደሆኑ ጎረቤቶቿ ሊረዱ እንደሚገባ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ በህጋዊ እና ሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ እየሰራች እንደምትገኝም ተናግረዋል።
የባህር በር ጉዳይ የፖለቲካ አጀንዳ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው ብለዋል።
የባህር በር አለመኖር በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሚገኝ ገልጸው ጉዳዩ አፈጣኝ መፍትሄ እንደሚያሻው አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚፈያስፈልጋት እና ይህም በንግድ ህጎች አማካኝነት ምላሽ ያገኛል ብለው እንደሚያምኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።