በኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 1 መቶ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመንገድ ሽፋን 1 መቶ 75 ሺህ ኪሎ ሜትር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል፡፡
በድምሩ 3 መቶ የሚሆኑ ፕሮጀክቶች መፅደቃቸውን ያብራሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አጠቃላይ ወጪውም 1.5 ትሪሊየን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከፀደቁ ፕሮጀክቶችም ውስጥ 169 ገደማ የሚሆኑትና 11 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ግንባታ መጀመሩንና በዘንድሮው በጀት ዓመትም 1 ሺህ ኪሎ ሜትሩ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ 17 ሺህ ኪሎ ሜትር የሚይዙ 145 የጥገና ፕሮጀክቶችም እንደተጀመሩ እና በመገባደድም ላይ ያሉም እንዳሉ አብራርተዋል፡፡
በሚካኤል ህሩይ