የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ዉሳኔዎችን አሳለፈ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ ዉሳኔዎችን አሳለፈ

AMN ነሃሴ 9/2017

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 5ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ስብሰባዉን አካሄዷል።

ካቢኔዉ በዛሬዉ ዉሎዉ በቀረቡት 4 የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ዉሳኔዎችን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

1ኛ ራስን ችሎ የሚለማ ቦታ ዝቅተኛው ስፋትና የፊት ለፊት ገፅታ ርዝመት ( set back) አተገባበር ጥናት ላይ ተወያይቶ የከተማዋን እድገት ታሳቢ ያደረገ እና የአተገባበር ምቹነት ታሳቢ ባደረገ የቀረበዉ ጥናት ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

2ኛ በኮሪደር ልማት የለሙ ልዩልዩ መሰረተ ልማቶች እና የወንዝ ዳርቻ ልማት አስተዳደር ባለስልጣን ለማቋቋም የቀረበዉ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ የማስተዳደር ፣ አገልግሎት የመስጠት፣የመጠበቅ ፣የማስተባበር እና የማቀናጀት ኃላፊነት እንዲኖረው ሆኖ እንዲቋቋም ውሳኔ አሳልፏል፡፡

3ኛ የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ አስተዳደር አግባብነት ያለዉ አካል ሳይፈቅድ ፤ የተያዙ ይዞታዎች አገልግሎት የመስጠት ጊዜን ለማራዘም በቀረበ የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

4ኛ. አገራዊ ፋይዳ ላላቸው ፕሮጀክቶች እና የኢንዱስትሪ ልማት ተቋማት ላይ ለመሳተፍ የቀረበ የመሬት ጥያቄ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review