በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞቸ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ መሆኑን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞቸ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ መሆኑን አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ
  • Post category:ልማት

AMN – መስከረም 7/2018 ዓ.ም

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞቸ የተካሄደው የህዳሴ ግድብ የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ ተፈጥሮን እንደ ዐይኑ ብሌን መንከባከብ እና ማልማት ለሚያውቀው የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ሕዳሴ ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል።

ውሃ ለኦሮሞ በሕይወቱ፣ በባህሉ፣ በታሪኩ እና በሕዝባዊ እሴቶቹ ሁሉ ትልቅ ቁርኝት ያለው የማንነት ቀለሙ መሆኑንም ገልፀዋል።

በታላቁ ወንዛችን ዓባይ ላይ ለተገነባው የህዳሴ ግድብ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞቸ የተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ከደስታ የተሻገረ በመተባበር የመፈጸም አቅምን የሚያሳይ ነው።

በድጋፍ ሰልፎቹ በተስተጋቡት ድምጾችም ልማትን የመናፈቅ ሰላምን አብዝቶ የመፈለግ፣ በመደመር የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመንን በብዙ ድሎች የማጽናት ብርቱ መሻቶች እንደሆኑ አይተናል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review