የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ በውስጥ ለውስጥ የተዘረጉ የመንገድ መብራቶች ጨለማን ተገን አድርገው የፈፀም የነበረን ንጥቂያና ዝርፊያን ጨምሮ ለህብረተሰቡ የደህንነት ስጋት የሆኑ ወንጀሎች መቀነስ ችለዋል ቀንሰዋል ሲሉ ተናገሩ፡፡
ወይዘሮ ሊዲያ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የውስጥ ለውስጥ የመንገድመብራት ዝርጋታን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
የውስጥ ለውስጥ መብራቶች ጨለማን ተገን ተደርጎ የሚፈፀም ወንጀልን ለመከላከልና የከተማዋን የሰላም ሰራዊት ስራን በማቅለል እገዛቸው ከፍ ያለ ስለመሆኑም ኃላፊዋ አንስተዋል።
መብራቶቹ ለህብረተሰቡ የደህንነት ስጋት የሆኑ ችግሮችን በመቅረፍ ሚናቸው ትልቅ ስለመሆኑ ያነሱት ወይዘሮ ሊዲያ ሰላምን ማስጠበቅ የዘመቻ ስራ ሳይሆን ቀጣይነት ባለው መልኩ የሚተገበር ስለመሆኑም አስገንዝበዋል።

ከአሁን በፊት በአራት ክፍለ ከተሞች ያለውን የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር መብራቶችን ለማየት ተሞክሯል ያሉት ወይዘሮ ሊዲያ የውስጥ ለውስጥ መብራቶች መንገዶችን በብርሃን በመሸፈን ዝርፊያና ንጥቂያን ጨምሮ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን እንዲቀንሱ አድርገዋል ብለዋል።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የተሰራው ስራ ከተማዋን ከማስዋብና ከማድመቅ የተሻገረ ዓላማ ያለው ና የከተማዋን አስተማማኝ ሰላም የሚያረጋግጥ ነውም ብለዋል።
ተግባሩ ለሌሎች ክፍለ ከተሞች ልምድና ተሞክሮ የሚወስዱበት እንደሆነም ተመላክቷል።
በፂዮን ማሞ