ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰውስራሽ አስተውሎት ዘርፍ ለመሰማራት ሃሳብ እና ፍላጎት ኖሯቸዉ በተለያየ ምክንያት እድሉን ያላገኙ የከተማዋ ታዳጊዎችና ወጣቶች በተመቻቸዉ የነፃ እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቀረቡ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰውስራሽ አስተውሎት ዘርፍ ለመሰማራት ሃሳብ እና ፍላጎት ኖሯቸዉ በተለያየ ምክንያት እድሉን ያላገኙ የከተማዋ ታዳጊዎችና ወጣቶች በተመቻቸዉ የነፃ እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቀረቡ

AMN ህዳር 11/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሰውስራሽ አስተውሎት ዘርፍ ለመሰማራት ሃሳብ እና ፍላጎት ኖሯቸዉ በተለያየ ምክንያት እድሉን ያላገኙ የከተማዋ ታዳጊዎችና ወጣቶች በተመቻቸዉ የነፃ እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለኢትዮዽያዊያን የኩራት ምንጭ እንዲሆን ተደርጎ የተገነባዉን የኢትዮዽያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤትን የጎበኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባለፉት የለውጥ አመታት በአገራችን ከታዩ የማድረግ አቅሞች መካከል አንዱ የሁሉም ፣ በሁሉም የሆነችዉ የአዲሷን ኢትዮዽያ ተልዕኮ መሸከም የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት ነዉ ብለዋል።

የተቋማት ግንባታ ማሳያው ደግሞ የኢትዮዽያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እንዱ ነው ። አጠቃላይ በተቋሙ የተመለከትነዉ ሁሉ እጅግ አስደናቂ ነዉ።

በዚህ የዉድድር አለም እንደ አገር ሉአላዊነትን አስጠብቆ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቆየት በየትኛዉም መስፈርት የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል ።

ይህንን እዉነታ ከአመታት በፊት አስቀድሞ በመረዳት ለዚህም አገራዊ ተልዕኮን በብቃት የሚያሳካ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አቅም ያለዉ ተቋም በአጠረ ጊዜ እዉን እንዲሆን ላደረጉት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ለመላዉ የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት አመራሮችና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዘርፉ ለመሰማራት ሀሳብ ፣ ፍላጎት እያላችሁ በተለያየ ምክንያት እድሉን ያላገኛችሁ የከተማችን ታዳጊዎች ፣ ወጣቶች ተቋሙ ባመቻቸዉ የነፃ እድል እንድትጠቀሙ ጥሪ ማስተላለፋቸዉን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review