ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መከሩ

You are currently viewing ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት በሚያስችላቸው ጉዳይ ላይ መከሩ

AMN ሕዳር 11/2018

ኢትዮጵያና አዘርባጃን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን የሁለትዮች የጋራ ውይይት አድርገዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) እና በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በሁለትዮሽ በትብብር በሚሠሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይታቸው ላይም ፥ኢትዮጵያ የመከላከያ-ኢንዱስትሪ መሠረተ ልማቷን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ሚኒስትር አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) አስረድተዋል።

ሁለቱ ሀገሮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ በበኩላቸው፣ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።

ሀገራቸው ኢትዮጵያን የመከላከያ ኢንዱስትሪ አጋሯ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላትም ጠቁመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review