ሶስት ኢትዮጵያዊያን የኢጋድ ሚዲያ አዋርድ ተሸላሚ ሆኑ

You are currently viewing ሶስት ኢትዮጵያዊያን የኢጋድ ሚዲያ አዋርድ ተሸላሚ ሆኑ
  • Post category:አፍሪካ

AMN – ሕዳር 21/2018 ዓ.ም.

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት ለ3ኛ ጊዜ ባዘጋጀው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ሽልማት ሥነ-ሥርዓት በስካይ ላይት ሆቴል በዛሬው ዕለት በድምቀት ተካሂዷል።

“ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ የማይበገርና የተረጋጋ ክልል እንዲኖረን ስለአየር ንብረት ለውጥ ተግባር እንናገር!” በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው የዘንድሮው ሽልማት፣ በድምሩ 20 ዕጩዎች በ11 ዋና ዋና የሥራ ዘርፎች የክብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በመድረኩ ላይ ከፍተኛ ትኩረት የሳበው የሕይወት ዘመን ስኬት ሽልማት ሲሆን ሽልማቱ ለሁለት አንጋፋ የሚዲያ ባለሙያዎች ተበርክቷል – ከሱዳን ለጋዜጠኛ ፌይሰል መሐመድ እና ከኢትዮጵያ ደግሞ ለጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ።

በሌሎች ዘርፎች ሽልማት ያገኙ የሚዲያ ባለሙያዎችም ቀጣናዊ ውክልና የነበራቸው ሲሆን፣ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችም ሽልማት አግኝተዋል።

• በቴሌቪዥን ፕሮዳክሽን ዘርፍ: ለደማ (ኬንያ) እና መሐመድ ኑር መሐመድ (ሶማሊያ)

• በሬዲዮ ዘርፍ: ስቲቭ ሞካያ (ኬንያ) እና ዋምቢ ማይክል (ዩጋንዳ)

• በሕትመት ዘርፍ: ሙጋንድ ሜርያንን (ኬንያ) እና አምብሮስ ኦክዋንጌ (ዩጋንዳ)

• በዲጂታል ዘርፍ: ጌትነት ሸንቁጤ (ኢትዮጵያ) እና ገብሬል ጌትሉዋክ ዋል (ደቡብ ሱዳን)

• በማሕበራዊ ሚዲያ ዘርፍ: አሚና ኢዳን (ጅቡቲ) እና አህመድ መሐመድ (ሶማሊያ)

• በፎቶግራፍ ዘርፍ: አብዲራህማን ሰላድ (ሶማሊያ) እና አንድሪው ንጌአ (ኬንያ)

• ጾታን ያማከለ ዘገባ በመሥራት: አይባሬ ሲንደሬላ (ዩጋንዳ) እና ጀሚላ መሐመድ (ኬንያ)

• በአገር በቀል ቋንቋዎች ዘርፍ: ሂፓ አብደላዜም (ሱዳን) እና ሽመክት ለገሠ (ኢትዮጵያ)

• የዓመቱ ምርጥ የሚዲያ ሰው: ቦንፌስ ባራሳ (ኬንያ) እና አኒስቴሺያ ኪራጉ (ኬንያ)

የኢጋድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) እና የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በክብር እንግድነት ተገኝተው የሚዲያ ባለሙያዎች በአየር ንብረት ለውጥ ትግል ውስጥ ያላቸውን ወሳኝ ሚና አጉልተው የተናገሩ ሲሆን ኢትዮጵያም “የአፍሪካ አረንጓዴ ሻምፒዮን” መሆኗን ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review