ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሀይማኖት ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሀይማኖት ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀረበ

AMN ህዳር 23/2018

ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሀይማኖት ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሀይማኖት ተቋማት እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የላቀ ተሳትፎ ለሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በዚህ መድረክ እንዳሉት ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው፤ በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለምክክሩ ስኬትና ውጤታማነት በባለቤትነት ስሜት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የሀይማኖት ተቋማት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እስካሁን ከኮሚሽኑ ጋር በመሆን ለሰሩት ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የሀይማኖት ተቋማትና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ እና ወደፊትም በአብሮነት በመስራት ሀገራዊ ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በመድረኩ ባለፉት ዓመታት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ የተሰሩ ስራዎች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች አቅርበዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review