AMN-ሕዳር 27/2018 ዓ.ም
“በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እና አባላት ሲሰጥ በነበረዉ ሶስተኛ ዙር ስልጠና ላይ ሲሳተፉ የነበሩ አመራሮች በከተማዋ የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ኤ ኤም ኤን ያነጋገርናቸው አመራሮች በስልጠናው በንድፈ ሀሳብ ሲወስዱ የነበሩትን በመስክ ምልከታው በተግባር በማየታቸው መነሳሳትን እንደፈጠረባቸው አንስተዋል።
በቀጣይ የተሻለ ተግባር ለመፈፀም የሚያግዘን ነው ብለዋል። የተሰሩት የልማት ስራዎች የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡት ናቸው ብለዋል።
በከተማ ደረጃ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንደ ሀገር ልምድ የሚወሰድባቸው ናቸው ያሉት አመራሮቹ ከስልጠናው በኋላ ያዩትን ነገር ለማስፋት አቅም እንደሚጨምርላቸው ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል ።
አመራሮቹ አራዳ ፓርክ የኢሬቻ ፓርክ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አዲስ መሶብ በሳይንስ ሙዚየም ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታልንእና ጀርመን አደባባይ የተገነቡ ቤቶች ላፍቶ ቁጥር 2 የገብያ ማዕከል እና ጎብኝተዋል።
በመሀመድኑር ዓሊ