በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ከጨለማ ወደ ብርሃን የተቀየሩ ሞዴል ብሎኮች እና ቀጣናዎች የከተማዋን ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ያረጋገጡ ናቸው

You are currently viewing በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ከጨለማ ወደ ብርሃን የተቀየሩ ሞዴል ብሎኮች እና ቀጣናዎች የከተማዋን ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ያረጋገጡ ናቸው

AMN ታህሳስ 4/2018

በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ከጨለማ ወደ ብርሃን የተቀየሩ ሞዴል ብሎኮች እና ቀጣናዎች የከተማዋን ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ያረጋገጡ መሆናቸውን የአዲስ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለጹ።

በቢሮ ኃላፊዋ የተመራ የከተማና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ቡድን በወረዳዎች በምሽት ተንቀሳቅሰው ከጨለማ ወደ ብርሃን የተቀየሩ ሞዴል ብሎኮችን እና ቀጠናዎችን እንዲሁም የሰላም ሰራዊቱን የስራ እንቅስቃሴም በመጎብኝት፣ አበረታተዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6፣7 እና ወረዳ 14 የጎበኙ ሲሆን በህብረተሰቡ ከፍተኛ ተሳትፎ ከጨለማ ወደ ብርሃን የተቀየሩ ሞዴል ብሎኮችን እና ቀጠናዎች የከተማዋን ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ያረጋገጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ የሰላም ባለቤት በመሆን ሰፈሩን፣ ብሎኩን፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በአጠቃላይ አካባቢውን ብርሃናማ በማድረግ ፣ ካሜራዎችን በመትከል የሚከሰቱ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በእጅጉ መቅረፍ መቻሉ የሚደነቅ ነው ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ይህን አጠናክሮ መቀጠልና ተሞክሮውን ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እሸቱ ለማ (ዶ/ር) በበኩላቸው በክፍለ ከተማው ከጨለማ ወደ ብርሃን የተቀየሩ ሞዴል ብሎኮችን እና ቀጠናዎችን ተሞክሮ ለማስፋፋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በይታያል አጥናፉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review