የግል ተበዳይን እንሸኝሽ ብለዉ ተሽከርካሪ ውስጥ በማስገባትና በስለት በማስፈራራት ሞባይል ስልክና የአንገት ሀብል የወሰዱ ተጠርጣሪዎች ከእነ ተቀባዩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing የግል ተበዳይን እንሸኝሽ ብለዉ ተሽከርካሪ ውስጥ በማስገባትና በስለት በማስፈራራት ሞባይል ስልክና የአንገት ሀብል የወሰዱ ተጠርጣሪዎች ከእነ ተቀባዩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN ታኅሣሥ 06/2018 ዓ.ም

አማኑኤል ለውጤ እና አሉላ ተመስገን የተባሉ ተጠርጣሪዎች የግል ተበዳይ ብሌን አበባ የተባለች ግለሰብን እንሸኝሻለን በማለት ካሳፈሯት በኋላ ግለሰቧ ላይ የውንብድና ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩት ህዳር 14 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ሩዋንዳ ድልድይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 8:30 ገደማ ነው ።

የግል ተበዳይ ወይዘሮ ብሌን አበበ የተባለች አምሽታ ወደ ቤቷ ለመሄድ መንገድ ላይ እየተንቀሳቀሰች ሳለ ተጠርጣሪዎቹ እንሸኝሽ በማለት የሠሌዳ ኮድ 3 A91961አ/አ ቪትስ የሆነ ተሽከርካሪ ውስጥ ያስገቧታል።

ትንሽ እንደተንቀሳቀሱ ወደ ሩዋንዳ ድልድይ አካባቢ ሲደርሱ አማኑኤል ለውጤ የተባለው ተጠርጣሪ ድንገት ቢላ በማውጣት እያስፈራራ በወቅቱ በእጇ ይዛ የነበረውን 2 ሞባይል ስልኮች እና የብር የአንገት ሀብል አጠቃላይ ግምቱ 28 ሺህ ብር የሚያወጣ ይቀበሏታል።

በኋላ የስልኳን ሚስጥር ቁጥር በማስከፈት የሞባይል ባንኪንግ እና የቴሌ ብር ተጠቀሚ መሆኗንና አለመሆኗን ከአረጋገጡ በኋላ ገፍትረው ጥለዋት ከአካባቢው ይሰወራሉ ።

ከግል ተበዳይ ወይዘሮ ብሌን አበበ አቤቱታ የደረሰው የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የአየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጭምር ተጠርጣሪዎች ሲጠቀሙበት የነበረውን ተሽከርካሪ ሠሌዳን ለመለየት ችሏል።

ፖሊስ ባደረገው ተጨማሪ ምርመራን የማስፋት ተግባር ከተጠርጣሪዎቹ ንብረቱን የሚቀበል ሙስጠፋ ረዲ የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል።

በተሽከርካሪው ላይ በተደረገው ተጨማሪ ፍተሻም 6 ሞባይል ስልኮች፣ 2 ታብሌቶች፣ የብረት መቁረጫ መጋዝ፣ ኤርፎን ጨምሮ 2 የሴት ቦርሳ እንደተገኘ ከአየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

አንደንድ ግለሰቦች እንሸኛችሁ በማለት መሠል ወንጀሎችን እንደሚፈፀሙ ህብረተሰቡ በመረዳት የግለሰቦችን ማንነት ሳይገነዘብ ፈቃደኛ መሆን ለተመሣሣይ የወንጀል ድርጊት ሊዳርግ ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስአበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ መልዕክቱን አስተላልፏል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review