AMN – ታኅሣሥ 6/2018 ዓ.ም
በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ለመጠቀም በጋራ መስራት አለብን ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ተናገሩ ፡፡
በብሄራዊ ጥቅም የማይደራደር ትውልድ ለመፍጠር የጥበብ ስራዎችን ከፍተኛ አበርክቶ አላቸው ፣ ይህንን ለማሳካት የጥበብ ቤተሰብ ኃላፊነት መወጣት አለበት ብለዋል ሚኒስትሯ ።
የምንፈልገውን አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት የጥበብ ስራዎችን እንጠቀማለን ለዚህም የጥበብ ባለሙያዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባችሁ ብለዋል ።
የምንፈልገውን አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት እና ሕብረ ብሄራዊ አንድነት ለማጎልበት የጥበብ ስራዎችን እንጠቀማለን ለዚህም በኪነ-ጥበብ ዘርፍ ኢትዮጵያ ያላትን አቅም ለመጠቀም በጋራ መስራት አለብን ነው ያሉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ።
ኪን-ኢትዮጵያ በተለያዩ ዓለም አቀፋ ሀገራት ከሚያደርገው የኢትዮጵያን ባህልና እሴት የማስተዋወቅ ስራ በሀገር ውስጥም ሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ለማጠናከር በየክልሎች ይሰራል ብለዋል ።
ባህል በመጠበቅና የኢትዮጵያውያን እሴት በማጎልበት ሂደት ውስጥ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ባለሙያዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባችሁም ነው ያሉት ፡፡
የኪነ-ጥበብ ፈጠራዎች ስራዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም አንጻር ፣ የሥነ-ጥበብ ፈጠራ ስራዎችን ገዥ ትርክትን ከማስረጽ አንጻር ፣ እና የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ ላይ ከክልል እና ከፌዴራል የተውጣጡ የኪነ – ጥበብ ባለሙያዎች እና የክልል የባህል እና የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል ።
በተጨማሪም ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከኪነ-ጥበብ ፣ ከባህል እና ከስፖርት አንጻር በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በተመለከተ በውይይት መድረኩ ገለጻ ተደርጓል ።
በዳንኤል መላኩ