ኢትዮጵያ የ5ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ አዘጋጅ ሀገር ሆና ተመረጠች።

You are currently viewing ኢትዮጵያ የ5ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ አዘጋጅ ሀገር ሆና ተመረጠች።

AMN – ታኅሣሥ 7/2018 ዓ.ም.

ኢትዮጵያ 5ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ጨዋታ ውድድር ለማስተናገድ ያቀረበቸው ጥያቄ በአኖካ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በሙሉ ድምጽ ተቀባይነት ማግኘት ተችሏል።

ከ2 አመት በኋላ የሚደረገውን 5ኛውን የወጣቶች ኦሎምፒክ ለማስተናገድ ዕድሉን ማግኘቷ ሀገሪቱ በስፖርት መስክ ያላትን አቅም ለዓለም ለማሳየት ትልቅ ዕድል እንደሚሆንላት ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች ውድድርን ለማዘጋጀት ያገኘችው ተቀባይነት ከ2 ዓመት በኋላ የኮፕ 32 የአየር ንብረት ጉባዔን እንድታዘጋጅ በተመረጠች ማግስት መሆኑ ለሀገራችን ተጨማሪ ስኬት ሆኗል።

በዓለማየሁ ሙሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review