ተቋማትን በቴክኖሎጂ የማዘመን ተግባር የዲጅታል 2030 ኢትዮጵያ አካል ነው

You are currently viewing ተቋማትን በቴክኖሎጂ የማዘመን ተግባር የዲጅታል 2030 ኢትዮጵያ አካል ነው

AMN-ጥር 2/2018 ዓ/ም

ተቋማትን በቴክኖሎጂ የማዘመን ተግባር የዲጅታል 2030 ኢትዮጵያ አካል መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ (ዶ/ር) ጀማሉ ጀንበር አሰታወቁ።

የአዲስ አበባ ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በመዲናዋ የሚሰጡትን አገልግሎት ዲጅታል በማደርግ 53 የከነማ ፋርማሲዎች በአንድ ላይ የሚያስተሳስር መተግበሪያ በመፍጠር ወደ ተግብራ አስገብቷል።

በመርሃ ግብሩ ተቋማትን በቴክኖሎጂ የማዘመን ተግባር የዲጅታል 2030 ኢትዮጵያ አካል ከመሆን ባለፈ ስማርት ሲቲና ማህበረሰብን የመፍጠር አላማን የሚያሳካ መሆኑን ነው (ዶ/ር) ጀማሉ ጀንበር የገለጹት።

የአዲስ አበባ ኢኖቪሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ስራ አስኪያጅ (ዶ/ር) ቱሉ ጥላሁን በበኩላቸው ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸውን ዲጅታልና በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 አካል በመሆን አላማውን ማሳካት ይገባቸዋል ብለዋል።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተንኩዌይ ጆክ አክለውም ባለስልጣኑ በስሩ የሚገኙ ተቋማትን በቴክኖሎጂ የማዘመን ተግብራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በከነማ ፋርማሲዎች የሚስጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በማዘመን የመዲናዋን የጤና ቱሪዝም ተመራጭነት ከፈ የሚያደርግ መሆኑን ነው የተመላከተው።

በፋሲል ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review