በቀን 52 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

You are currently viewing በቀን 52 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ

AMN ጥር 05/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ውሃና ፍስሽ ባለስልጣን የምስራቅ ተፋሰስ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ አካል የሆነው እና በቀን 52ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሩን አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ውሃና ፍስሽ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሰርካለም ጌታቸዉ በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የተጀመረዉ ፕሮጀክት በዓለም ባንክ የብድር አገልግሎት በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡

ግንባታዉ በፈረንጆቹ ግንቦት 2027ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡

የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዉ ሲጠናቀቅ የየካ ፤ የቦሌና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችን የፍሳሽ በመስመር ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review