7ኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበክረን እንሰራለን – የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

You are currently viewing 7ኛው ዙር አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበክረን እንሰራለን – የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
  • Post category:ፖለቲካ

AMN ጥር 5/2018

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ከተማ አካሂደዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳቢና የእናት ፓርቲ ተወካይ አቶ ሠለሞን ታፈሰ ም/ቤቱ ባለፉት 6 ወራቶች የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታንና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታን ለማፅናት በፓርቲዎች መካከል የሚታዩ የአመለካከት እና የፖለቲካ ልዩነቶችን በማክበርና በመቻቻል በሀገር አቀፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተሳትፎ የሚያጠናክሩ፣ ዘላቂ ሠላምንና ደህንነትን የሚያፀኑ ሥራዎችን እና የዴሞክራሲ ባህል ግንባታን የሚያጠናክሩ ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን አውስተው፤ ቀጣዩ 7ኛ ዙር አገራዊና ክልላው ምርጫ ነፃ፣ፍትሐዊ፤ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የሚሠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አቶ ሠለሞን፣ በኦሮሚያ ክልል የጋራ ም/ቤት መስረተው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዢው ፓርቲ ብልፅግና ጋር በመተባበር ብሔራዊ ጥቅሞችን እና የአገረ መንግስት ግንባታ ሥራዎችን የሚያፀኑ ተግባራትን ጨምሮ በምርጫ ጉዳዮች ላይ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ኦሮሚያ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ኃላፊ እና የኦሮሚያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ኢዳኤ በበኩላቸው

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ የተፈጠሩላቸውን ምቹ ሁኔታዎችን እና መልካም አጋጣሚዎችን በመጠቀም የያዙትን የፖለቲካ ዓላማ በነፃነትና በሰላማዊ መንገድ ለማፅናት፤ አልፎም በጠንካራ አገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ውስጥ ፓርቲዎቹ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የኦሮሚያ ወጣቶች ማህበር የዘንድሮ ምርጫ በተያዘለት ግብ መሠረት እንዲጠናቀቅ ይረዳ ዘንድ “በምርጫ ሠላማዊነትና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና” ላይ በጉባኤው ለተገኙ ተሰብሳቢዎች ስልጠና ሰጥቷል።

በጋራ ምክር ቤቱ 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል 21 ተገኝተው ተሳታፊ ሆነዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review