የገንዘብ ሚኒስቴር እና ዓለም ባንክ የከተማ ምርታማ ሴፍቲኔትና ስራ እድል ፈጠራ ፕሮጀክትን ለማስፈጸም የሚውል የ250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰመሬታ ሰዋሰው እና የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ፈርመውታል።
ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የኢትዮጵያ መንግሥት በከተማ የሚኖሩ አነስተኛ ገቢ ያላቸዉን የህብረተሰብ ክፍሎች የኑሮ ሁኔታን ለማሻሻል እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶችን በሥራ ገበያው ውስጥ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረዉን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያግዝ መሆኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡