የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኢትዮጵያዊ ምግቦች የሚቀርቡበት ፌስቲቫል ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የአደባባይ በአላት በሚከናወኑበት በዚህ ወር የተዘጋጀው ጋስትሮኖሚ የተሰኘው ይህን ፌስቲቫል ኮሚሽኑ ጎልደን ግሩፕ ሆስፒታሊቲ ከተሰኘ ድርጅት ጋር ነው ያዘጋጀው ፡፡
የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ክፍት በሚሆነው በአይነቱ ለየት ባለው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያዊ ምግቦች ፣ የምግብ ግብአት አቅራቢዎች በሆቴሎችና በዘርፉ የተሰማሩ ከ100 በላይ ድርጅቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ እንደገለፁት የጥምቀት ከተራ በአልን አስታኮ በተዘጋጀው በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ የውጭ አገር ዜጎች የሚታደሙ ሲሆን ከ20 ሺህ በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡
ፌስቲቫሉ በሚሊኒየም አዳራሽ ጥር 9 እና 10 ለሁለት ቀናት ለህዝብ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሽመልስ ታደሰ