AMN – ጥር 15/2018 ዓ.ም.
ለልምድ ልውውጥ ወደ መዲናዋ ከመጡ የአፍሪካ ከተማ ከንቲባዎች እና የክልል አስተዳዳሪዎች ጋር በገቢዎች ቢሮ በቴክኖሎጂ እገዛ የተሰሩ የታክስ አሰባሰብ ለውጥና ሪፎርም ውጤቶችን በተመለከተ የልምድ ልውውጥ መካሔዱን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እንደገለጹት ከልምድ ልውውጡ ባሻገር የልዑካን ቡድኑ የእንጦጦ፣ ፒኮክና አራዳ ፓርኮችን ጨምሮ የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን አስጎብኝተው የሽኝት መርሐ ግብር አካሒደዋል።