AMN ጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም
አንደኛው የኢትዮጵያ 10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድር በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ዛሬ ረፋድ ላይ በድምቀት ተከናውኗል። በ173 አትሌቶች መሀከል በተደረገው ውድድር በወንዶች ሀጎስ ገብረ ሂወት ከኢትዮ ኤሌትሪክ አሸናፊ ሆኗል። ገመቹ ዲዳ ከኢትዮ ኤሌትሪክ 2ኛ ሲወጣ ፣ በግል የተወዳደረው አልዩ ቀሲም 3ኛ አጠናቋል።
በሴቶች በተደረገ ውድድር ደግሞ ቢቂሌ አንበሱ ከኦሮሚያ ፖሊስ ፣ ጉተኒ ሻንቆ ከኢትዮ ኤሌትሪክ እንዲሁም ሰውሃረግ ሃይማኖት ከኢትዮጵ ንግድ ባንክ ከአንድ እስከ ሦስት ወጥተዋል።
የውድድሩ አላማ ክልሎች ፣ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦች፣ ተቋማትና የግል ተወዳዳሪ አትሌቶች የውድድር ዕድል ለመፍጠር እንዲሁም ተተኪ አትሌቶችን ማፍራት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሶፊያ ሀሰን