የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ሰባቱ ዋና ዋና ግቦች የትኞቹ ናቸዉ?

You are currently viewing የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ሰባቱ ዋና ዋና ግቦች የትኞቹ ናቸዉ?
  • Post category:አፍሪካ

AMN ጥር 21/2018 ዓ.ም

የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ (Agenda 2063) ሰባቱ ዋና ዋና ግቦች

👉 የበለጸገች አፍሪካ፡- በአካታች እድገት፣ ድህነትን በማጥፋት እና በዘላቂ ልማት ላይ የተመሰረተች አፍሪካ፡፡

👉 የተቀናጀች አህጉር፡- በፖለቲካ የተዋሃደች፣ በፓን-አፍሪካኒዝም (Pan-Africanism) እሳቤዎች እና በአፍሪካ ህዳሴ ራዕይ ላይ የተመሰረተች አፍሪካ፡፡

👉መልካም አስተዳደር፡- ዲሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብቶች፣ ፍትህ እና የህግ የበላይነት የሰፈኑባት አፍሪካ።

👉 ሰላማዊ እና ደህንነቷ የተጠበቀ አፍሪካ፡- ሁሉንም ግጭቶች የማስወገድ ዓላማ ያላት አፍሪካ፡፡

👉 ባህላዊ ማንነት፡- ጠንካራ ባህላዊ ማንነት፣ የጋራ ቅርስ፣ የጋራ እሴቶች እና ስነ-ምግባር ያላት አፍሪካ።

👉 በህዝብ የሚመራ ልማት፡- በአፍሪካ ህዝብ በተለይም በሴቶች እና በወጣቶች አቅም ላይ የሚተማመን ልማት።

👉 ጠንካራ አለምአቀፋዊ ተዋናይ፡- አፍሪካ በአለም መድረክ ላይ የተባበረች፣ የጸናች እና ተጽእኖ ፈጣሪ አጋር ሆና መቅረብ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review