በመዲናዋ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈጽሙ የተገኙ 32 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing በመዲናዋ ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈጽሙ የተገኙ 32 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN – ጥር 23/2018 ዓ.ም.

በመዲናዋ በ19 ስጋ ቤቶችና በ6 የግንባታ ዕቃዎች መሸጫ ቤቶች ላይ በተካሔደ ኦፕሬሽን 32 ያለደረሰኝ ሽያጭ ሲፈጽሙ የተገኙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የግብር ስወራን ለመከላከልና የንግድ ሥርዓቱን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥ ባደረገው ኦፕሬሽን በ25 የንግድ ድርጅቶች ደረሰኝ ሳይቆርጡ ግብይት ሲፈጽሙ የተገኙ 32 በስጋ ቤትና በግንባታ እቃዎች ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ያለ ደረሰኝ የሽያጭ ተግባራትን ኪያከናወኑ የነበሩ የንግድ ባለቤቶችና ሠራተኞች መሆናቸውንም ቢሮው ገልጿል፡፡

ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት የኦፕሬሽን ስራውን ማካሄዱን የገለጸው ቢሮው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የመንግሰትን ጥቅም ለማሳጣት ከታክስ አስተዳደር አዋጅ በተጻረረ መልኩ ያለደረሰኝ ሽያጭ በመፈጸም ወንጀል ተጠርጥረው በአሁኑ ወቅት ጉዳያቸው በፖሊስ ተይዞ ለፍርድ የሚቀርቡ ይሆናል ብሏል፡፡

በቀጣይ ቀናትም ቢሮው የኦፕሬሽን ተግባሩን በሌሎችም ዘርፎች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን የንግዱ ማኅበረሰብ ግብይቶችን በደረሰኝ ብቻ እንዲፈጽም እና ኅብረተሰቡም በ7075 ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም መሰል ወንጀሎችን እንዲያጋልጥ ለኤ ኤም ኤን በላከው መረጃ ጥሪ አቅርቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review