ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አካላት ጋር እየተወያየ ነው

You are currently viewing ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አካላት ጋር እየተወያየ ነው
  • Post category:ፖለቲካ

ጥር 29/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በአማራ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ እና የሰላምን መንገድ መርጠው ከተመለሱ አካላት ጋር እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የመድረኩን ዓላማ በማስተዋወቅ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ቡድኑ ሰላምን በመሻት እና ኮሚሽኑ ሲያቀርባቸው የነበሩ የምክክር ጥሪዎችን በመቀበል ወደ ምክክር እና ሰላም መንገድ በመምጣታቸው አመስግነው ይህም ለሀገራችን ሰላም ትልቅ እምርታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽኑን በመወከል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕ/ር) የኮሚሽኑን አመሠራረት፣ ያከነወናቸውን ዐበይት ተግባራት፣ ስኬቶቹን እና ፈተናዎቹን እንዲሁም በቀሪዎቹ ጊዜያት የሚያከናውናቸውን ተግባራት አብራርተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ዋና ኮሚሽነሩ በአማራ ክልል የተከናወነውን የምክክር ሒደት በተመለከተም ገለጻ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ነፍጥ አሸናፊ እና ተሸናፊን የሚፈጥር እንጂ ሀገራዊ መግባባትን የሚያሰፍን እንዳልሆነ የገለጹት ዋና ኮሚሽነሩ ሀገራዊ መግባባት የሚሰፍነው ሁሉም አካላት ስለሀገራቸው ለመመካከር ባላቸው ጽኑ ፍላጎት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ ነፍጥ አንስተው ወደ ጫካ ያስገቧቸውን ጉዳዮች ጨምሮ ክልላዊና ሀገራዊ ፋይዳ የሚኖራቸውን አጀንዳዎችን አደራጅተው በዚሁ መድረክ ለኮሚሽኑ የሚያስረክቡ መሆኑን ለኤ ኤም ኤን በላከው መግለጫ ገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review