የአዲስ አበባ ከተማ በብልጽግና ዕሳቤና ስትራቴጂዎች በመመራቷ፣ የዘመናት የጎስቋላነት ገጽታዋን በመቀየር ወደ ብርሃናማ ምዕራፍ ተሸጋግራለች- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing የአዲስ አበባ ከተማ በብልጽግና ዕሳቤና ስትራቴጂዎች በመመራቷ፣ የዘመናት የጎስቋላነት ገጽታዋን በመቀየር ወደ ብርሃናማ ምዕራፍ ተሸጋግራለች- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – ጥር 29/ 2018 ዓ.ም

3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማ አስተዳደሩን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን፤ ባለፉት ስድስት ወራት በአማካይ 95.3 በመቶ አፈጻጸም መመዝገቡን ገልጸዋል።

ከንቲባዋ አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ ከለውጡ ወዲህ ግልጽ በሆነ የብልጽግና ዕሳቤና ስትራቴጂዎች በመመራቷ፣ ለዘመናት የቆየውን የኋላ-ቀርነትና የጎስቋላነት ገጽታ በመቀየር ወደ ተጨባጭ ብርሃናማ ምዕራፍ ተሸጋግራለች ብለዋል።

የተመዘገቡት ስኬቶች በድንገት የመጡ ሳይሆን በመንግሥት፣ በሕዝብና በግሉ ዘርፍ ቅንጅት እንዲሁም በ24/7 የሥራ መርሃ ግብር የተመዘገቡ የሐሳብና የላብ ውጤቶች መሆናቸውንም ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡

ይህም ሀገርን ወደ ከፍታ ማምጣት እንደሚቻል ትልቅ ተሞክሮ የተቀመረበት መሆኑም ተነስቷል።

ባለፉት ስድስት ወራት የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እቅድ በማክሸፍ የከተማዋ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ተደርጓል ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ በተመሳሳይ መሠረታዊ የመሠረተ ልማት ጉድለቶችን የሚቀርፉ ስር ነቀል የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን በሪፖርቱ አንስተዋል፡፡

አስተዳደሩ በሰው ተኮር መርሃ ግብሮች የነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ በመመልከት የዜጎችን እንባ ያበሰበት፣ የዘመሙ ጎጆዎችን በማቃናት ማኅበራዊ ፍትህን ያሰፈነበትና የሕዝብ አገልጋይነትን በተግባር ያረጋገጠበት ስድስት ወራት መሆኑንም ከንቲባ አዳነች አንስተዋል፡፡

የከተማዋን ገቢ በብቃት በመሰብሰብና ከብክነት በጸዳ መንገድ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን በጀት ለዘላቂ ልማት ማዋል መቻሉ የገለጹት ከንቲባ አዳነች፤ ይህም የከተማዋን ተወዳዳሪነትና ለነዋሪዎች ምቹ የመሆን ዕድል ከፍ አድርጎታል ብለዋል ።

ከንተባ አዳነች አክለውም አዲስ አበባን ውብ፣ ጽዱና አረንጓዴ በማድረግ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጎብኝዎች ደግሞ ሳቢና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

በአስማረ መኮንን

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review