የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሰላምና ደህንነት ስራዎችን የሚያሳልጡ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ አስገባ

You are currently viewing የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሰላምና ደህንነት ስራዎችን የሚያሳልጡ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ አስገባ

AMN — ጥር 30/ 2018 ዓ.ም

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከልና የነዋሪዎችን ደህንነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዘመናዊ የደህንነት ካሜራዎችን በ19 አደባባዮች ላይ በመትከል ወደ ስራ ማስገባቱን አስታወቀ።

የተተከሉት የደህንነት ካሜራዎች ጥራት ያላቸው ምስሎችን በቀጥታ ወደ መምሪያው የመረጃ ክፍል የሚያደርሱ ሲሆን፤ የግለሰቦችንና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ በቅርበት በመከታተል የክፍለ ከተማውን ሰላምና ደህንነት የሚያረጋግጡ ናቸው።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው እንደገለጹት፤ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች የፖሊስን ስራ የሚያቀላጥፉና የነዋሪዎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያረጋግጡ ናቸው።

ባለፉት ሶስት አመታት የወንጀል ድርጊት ይፈጸምባቸዋል ተብለው በተለዩ አካባቢዎች የፖሊስ ማዕከላትን በመክፈትና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ በተሰራው ስራ የወንጀል ድርጊቶችን መቀነስ መቻሉም ተገልጿል።

በክፍለ ከተማው በተከናወነው የቴክኖሎጂ ትውውቅ እና የእውቅና መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ፖሊስ መምሪያው በቀጣይም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የደህንነት ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በፈቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review