ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

You are currently viewing ዘጠነኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ዛሬ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

AMN የካቲት 9/2018

የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን(ኢሴኤ) ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሁነቱን አዘጋጅተውታል።

“የአፍሪካን መጻኢ ጊዜ በፋይናንስ መደገፍ፤ ስራ እና ኢኖቬሽን ለዘላቂ ትራንስፎርሜሽን” የፎረሙ መሪ ሀሳብ ነው።

የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአፍሪካ የልማት እና የኢኮኖሚ እድገት ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን በማድረግ በየዓመቱ የሚካሄድ ከፍተኛ አህጉራዊ የምክክር መድረክ መሆኑን ኢዜአ ከኢሲኤ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አህጉራዊው መድረክ የአፍሪካ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተዋንያንና የልማት አጋሮችን በአንድ መድረክ ያገናኛል።

ፎረሙ አጋርነትና የኢንቨስትመንት መጠንን ማሳደግ በተለይም የመንግስት እና የግል የተቀናጀ የፋይናንስ አቅርቦትን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ አማራጮችን ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ይወያያል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ሁነት ላይ የአፍሪካ ሀገራት የመሪዎች የምክክር መድረኮችና የባለሙያዎች ውይይቶች ይደረጋሉ።

አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችና የፈጠራ ባለሙያዎችን ከባለሀብቶች እና ፋይናንስ አቅራቢዎች ጋር የሚያገናኝ አውደ ርዕይም ይካሄዳል።

ሁነቶቹ ቃል ኪዳኖችን ወደ ተጨበጡ የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ለመቀየር አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል።

የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በዘላቂ ልማት ግቦችና በአጀንዳ 2063 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ስትራቴጂካዊ ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝም በመረጃው ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review