10 ደቂቃ በተቋረጠው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ቤኔፊካን አሸነፈ

You are currently viewing 10 ደቂቃ በተቋረጠው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ቤኔፊካን አሸነፈ

AMN የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ቤኔፊካን አሸንፏል።

በስታዲዮ ዳሉዝ በተደረገው ጨዋታ ቪኒሺየስ ጁኒየር ብቸኛውን ግብ በስሙ አስመዝግቧል። ብራዚላዊው ተጫዋች ግቡን ካስቆጠረ በኋላ ግን ጨዋታው ለ10 ደቂቃ ተቋርጧል።

ቪኒ ጁኒየር ከቤኔፊካው ተጫዋች ጂያንሉካ ፕሬኤስቲያኒ የዘረኝነት ጥቃት ደርሶብኛል ብሎ ሪፖርት በማድረጉ ፈረንሳዊው ዋና ዳኛ ፍራንሲዮስ ሌትዢየር ጨዋታውን አቋርጠዋል።

ጨዋታው ከ10 ደቂቃ በኋላ ተጀምሮ ተጨማሪ ግብ ሳይቆጠር በማድሪድ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በውጥረት ታጅቦ በተጠናቀቀው ጨዋታ በተከሰቱ ጋዳዮች ላይ የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በጥልቀት ማጣሪያ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌሎች ጨዋታዎች ፓሪሰን ዠርማ ሞናኮን 3ለ2 አሸንፏል። ለባለፈው ዓመት የውድድሩ አሸናፊ ፓሪሰን ዠርማ ዴዚሪ ዱኤ ሁለት ግብ ሲያስቆጥር ፣ አችራፍ ሃኪሚ ሌላኛውን አክሏል።

አማካዩ አሌክሳንደር ጎሎቪንን በቀጥታ ቀይ ካርድ ላጣው ሞናኮ ፎላሪን ባሎጎን ሁለቱን ግቦች ማስቆጠር ችሏል።

ቦሩሲያ ዶርትመንድ በሴርሁ ጉይራሲ እና ማክሲሚሊያን ቢር ግቦች አታላንታን 2ለ0 ረቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review