ኢትዮጵያውያን በድህነት እና ኋላ ቀርነት ላይ በመዝመት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል

You are currently viewing ኢትዮጵያውያን በድህነት እና ኋላ ቀርነት ላይ በመዝመት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል

የካቲት 19/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያውያን በድህነት እና ኋላ ቀርነት ላይ በመዝመት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸዉ በብልጸግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጸህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተሻለ እምርታ እያስመዘገቡ ከሚገኙ ዘርፎች መካከል የከተማ ግብርና ይጠቀሳል፡፡

በዘርፉ የሚሰራው ስራ አሁንም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አርሶአደር እና ከተማ ግብርና ጸህፈት ቤት 4ኛ ዓመት 3ኛ ዙር የሌማት ትሩፋት ንቅናቄ መርሃ ግብር ተካሂዷ፡፡

በዚሁ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት በብልጸግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጸህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ኢትዮጵያውያን በድህነት እና ኋላ ቀርነት ላይ በመዝመት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚገባቸዉ ገልጸዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም የሌማት ትሩፋት የስራ ባህልን በመቀየር እና የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ኮሚሽን ኮሚሸነር ባዩ ሸጉጤ የሌማት ትሩፋት መርሃግብር የተሳሳተ አተያይን ያስተካከለ መሆኑን ጠቁመው ባለፉት የለውጥ ዓመታት በአዲስ አበባ ከተማ በዘርፉ ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ቁጥር ከ 1.2 ሚሊየን መሻገሩን ገልጸዋል፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በሌማት ትሩፋት የተሰሩ ስራዎች የከተማዋን የምግብ ዋስትና መደገፍ መቻሉን ገልጸው በክፍለ ከተማ ደረጃ ከ114 ሺ በላይ ዜጎችን በዘርፉ ተሳታፊ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል፡፡

አዳዲስ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎች በበኩላቸው በተደረገላቸው ነገር የተሰማቸው ደስታ ገልጸው በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ወደ ዘርፉ የተቀላቀሉ አዳደስ የከተማ ግብርና ተሳታፊዎች በስራቸው ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ከተማ አስተዳደሩ የጀመረውን ስራ መደገፍ እንደሚገባቸው ተመላክቷል፡፡

በሃብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review