ከትግራይ ሕዝብ ተነጥሎ ብቻዉን የቀረዉ እና የተከፋፈለዉ ቆሞ ቀሩ የሕወሃት ቡድን በተዳከመ ኃይል ጸረ ኢትዮጵያ ከሆኑ ኃይሎች ጋር ተሰልፎ ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ይገኛል

You are currently viewing ከትግራይ ሕዝብ ተነጥሎ ብቻዉን የቀረዉ እና የተከፋፈለዉ ቆሞ ቀሩ የሕወሃት ቡድን በተዳከመ ኃይል ጸረ ኢትዮጵያ ከሆኑ ኃይሎች ጋር ተሰልፎ ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ይገኛል

AMN የካቲት 25/2018 ዓ.ም

ቆሞ ቀሩ የሕወሃት ቡድን በትግራይ ሕዝብና በድርጅቱ አመራሮችና አባላት ላይ የነበረዉ ተስፋ በመዳከሙ ጸረ ኢትዮጵያ ከሆኑ ኃይሎች ጋር ተሰልፎ ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቆይታ ህወሃት አሁን ላይ ያለበትን አጠቃላይ ሁኔታ በስፋት አብራርተዋል፡፡

ቆሞ ቀሩ የሕወሃት ቡድን የትግራይን ሕዝብም ሆነ የደርጅቱን አመራሮችና አባላት የማይወክል መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡድኑ በአመራርና አባላቱ ተከፋፍሎ ከሕዝብ ተነጥሎ ብቻዉን ቀርቷል ብለዋል፡፡

ቡድኑ በአባላቱና በሕዝቡ ላይ የነበረዉ ተስፋ በመዳከሙ፤ ተስፋዉን ወደ ዉጭ ኃይሎች በማድረግ ባለችዉ አቅም ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ በተለይ ወጣቱና ታጣቂዎች ጦርነት አንፈልግም ማለታቸዉን እያየን ነዉ ፤ ይህ ጉዳይ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች መስፋት ያለበት ጉዳይ ነዉ ብለዋል፡፡

ቆሞ ቀሩ የሕወሃት ቡድን በአባላቱና በሕዝቡ ላይ የነበረዉ ተስፋ እየተዳከመ ሲመጣ ተስፋዉን ወደ ዉጭ ኃይሎች ማድረጉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቡድኑ በተዳከመ ኃይል ወታደራዊ ቅስቀሳዎችን እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከትግራይ ሕዝብ ተነጥሎ ብቻዉን የቀረዉ እና የተከፋፈለዉ ቆሞ ቀሩ የሕወሃት ቡድን የፌደራል መንግሥት ለልማት የሚልክለትን በጀት እየነጠቀ የጣታቂዎችን የሚቀልብ ቡድን ወደመሆንም ተሸጋግሯል፡፡

በወንድማገኝ አሰፋ

#addismedianetwork

#VoiceOfGenerations

#peace

#security

#addisababa

#Ethiopia

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review