AMN – የካቲት 25/2018 ዓ.ም.
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሕዝበ ሙስሊም ጋር የአብሮነት መገለጫ በሆነችው በውቧ አራዳ ፓርክ የኢፍጣር መርሐ-ግብር አካሒደዋል።
በአሁኑ ወቅት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በታላቁ የረመዳን ጾም፣ የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ደግሞ በታላቁ ዐቢይ ጾም ወደ ፈጣሪ ይበልጥ የሚቀርቡበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።
ከወትሮው በተለየ ይህ ወቅት ያለ ሃይማኖት ልዩነት እርስ በእርስ የምንጠያየቅበት፣ የምንደጋገፍበት፣ የምንተሳሰብበትና ‘ምን ጎደለ?’ የምንባባልበት ልዩ ጊዜ መሆኑንም ከንቲባዋ አስታውቀዋል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ወገኖች ጋር የሚደረገዉ የኢፍጣር ፕሮግራም በሁሉም የከተማዋ ክፍለ ከተሞች በስፋት እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው የገለጹት።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ከተማችንን የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ተምሳሌት የማድረጉ ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።