የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተዘጋጀ አዲስ የኅብር ዜማ አስተዋወቀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተዘጋጀ አዲስ የኅብር ዜማ አስተዋወቀ

AMN – የካቲት 25/2018 ዓ.ም.

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ “ምርጫችን ነው – ሀገር ያለእኛ” የሚል ስያሜ ያለውን ኅብረ ዜማ አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ቦርዱ በሀገሪቱ ነጻ፣ ፍትሐዊና ገለልተኛ የሆነ ስኬታማ ምርጫ እንዲከናወን በተለያዩ መስኮች በትኩረት እየሠራ ስለመሆኑ አንስተዋል።

ቦርዱ ዜጎች በምርጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማነሳሳትና ግንዛቤ መፍጠር ቀዳሚ ተግባሩ ስለመሆኑ የገለጹት ሰብሳቢዋ በዛሬው ዕለት የተመረቀው ኅብረ ዜማም በዋናነት የምርጫ ሒደት ሰላማዊነት፣ የዜጎችን የባለቤትነት ስሜት እና በምርጫ መሳተፍ ለሀገረ መንግስት ግንባታ ያለውን አስፈላጊነት የሚያጎሉ መልዕክቶችን የያዘ ነው።

ኪነጥበብ ሀሳቦችንና መልክቶችን በቀላሉ በሰዎች ልብ ውስጥ የማስረጽ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ይህ ኅብረ ዜማም ዜጎች በምርጫ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማነሳሳትና ግንዛቤ የመፍጠርን ዓላማን ይዟል ብለዋል።

የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የዕጩዎች ምዝገባ ከጥር 1 እስከ የካቲት 16 ሲከናወን መቆየቱን አስታውሰው በቅርቡም የዕጩዎች ዝርዝር ይፍ?ፋ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

ይህንን ተከትሎም የጠቅላላ ምርጫው የመራጮች ምዝገባ የፊታችን የካቲት 28 ለመጀመሪያ ጊዜ በዲጂታል ስርዓት እንደሚጀመር የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ተናግረዋል።

በኅብር ዜማው የማስተዋወቂያ ሥነ ስርዓት ላይ የቦርዱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት፣ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በራሔል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review