የጉለሌ ክፍለ ከተማን የለውጡ ትሩፋት ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በስኬት መከናወናቸው ተገለጸ

You are currently viewing የጉለሌ ክፍለ ከተማን የለውጡ ትሩፋት ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በስኬት መከናወናቸው ተገለጸ

AMN- የካቲት 26/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የሕዝብ ቅሬታዎችን የፈቱ፣ የኑሮ ውድነትን ያረጋጉና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ጉለሌን የለውጡ ትሩፋት ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በስኬት መከናወናቸው ተገለጸ፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማን በመወከል የህዝብ ተወካዮችና የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤቶች ተመራጮች ከመረጣቸው የሕብረተሰብ ክፍል ጋር ውይይት እያካሄዱ ነው።

በውይይት መድረኩ የክፍለ ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የሕዝብ ቅሬታዎችን የፈቱ፣ የኑሮ ውድነትን ያረጋጉና የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ጉለሌን የለውጡ ትሩፋት ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት በስኬት መከናወናቸውን አስታውቀዋል።

ነዋሪውን መሠረት ያደረጉ አስተማማኝ የጸጥታ ማስከበር ተግባራት፣ ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ ገበያን በማረጋጋት የኑሮ ውድነትን በተጨባጭ መቀነስ ያስቻሉ ሥራዎች እንዲሁም የኮሪደርና የወንዞች ዳርቻ ልማት መከናወናቸውን አመላክተዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም ባለፉት አምስት ዓመታት ከ204 ሺህ በላይ የሥራ ዕድሎች መፈጠራቸውን ጠቁመዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ መኩሪያ ጉርሙ፤ አስተዳደሩ ከነዋሪዎች ጋር በቅንጅት በመሥራቱ ቀደም ሲል የነበረውን የጸጥታ ሥጋት መቀነስ መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም ነዋሪዎች በምሽትም ጭምር እንደፈለጉ ተዘዋውረው የሚሠሩባትና ለኑሮ የተመቸች ክፍለ ከተማ መፍጠር ተችሏል ብለዋል።

ለተገኙት ስኬቶች በፓርላማም ሆነ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተወከሉ ተመራጮች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል።

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review