የዲጂታል መራጮች ምዝገባ የሚካሄደው አስቀድመው ለዚህ ተግባር በተለዩ ውስን ጣቢያዎች ብቻ ነዉ – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

You are currently viewing የዲጂታል መራጮች ምዝገባ የሚካሄደው አስቀድመው ለዚህ ተግባር በተለዩ ውስን ጣቢያዎች ብቻ ነዉ – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ

AMN የካቲት 29/2018

የዲጂታል መራጮች ምዝገባ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሳይሆን በተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ብቻ የሚከናወን መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታዉቋል።

ቦርዱ የዲጂታል መራጮች ምዝገባን አስመልክቶ በሰጠዉ ማብራሪያ መጪውን ምርጫ ግልጽ፣ ተዓማኒ እና ቀልጣፋ ለማድረግ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሳደግ አንዱ የሪፎርም አካል መሆኑን ገልጿል።

በዚህም መሠረት የዲጂታል መራጮች ምዝገባ ሥርዓትን በሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅቶች ተጠናቀው ወደ ተግባር ተገብቷል።

ይሁን እንጂ፣ የተጀመረው የዲጂታል መራጮች ምዝገባ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ሳይሆን በተመረጡ ጣቢያዎች ላይ ብቻ የሚከናወን መሆኑን ቦርዱ በድጋሚ ገልጿል።

መራጮች ሊገነዘቧቸው ከሚገባ ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም የዲጂታል ምዝገባው የሚካሄደው አስቀድመው ለዚህ ተግባር በተለዩ ውስን ጣቢያዎች ብቻ ነዉ።

በዲጂታል ምዝገባ በማይካሄድባቸው ሌሎች ጣቢያዎች ሁሉ፣ የመራጮች ምዝገባ እንደተለመደው በመዝገብ (በማኑዋል) የሚቀጥል ይሆናል።

መራጩ ሕዝብ መረጃዎችን ከቦርዱ ይፋዊ የመረጃ ምንጮች ብቻ በመከታተል፣ ለምዝገባ ሂደቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ቦርዱ ጥሪዉን አቅርቧል።

የዲጂታል መራጮች ምዝገባ የሚከናወንባቸውን የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ቀጣዩን ሊንክ በመጫን ማግኘት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review