7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ

You are currently viewing 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሠላማዊና ፍትሐዊ እንዲሆን ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – ሸይኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ

AMN – የካቲት 28/2018 ዓ.ም

6ኛው ታላቁ የጎዳና ላይ የኢፍጣር ሥነ-ስርዓት “ነጃሺ ለሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተካሒዷል።

በኢፍጣር መርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ዑስታዞች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ባስተላለፉት መልዕከት፣ሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ጾምን ሲያስብ ወደ ፈጣሪ ስለሀገር ሠላም አበክሮ በመጸለይ መሆን ይገባዋል ብለዋል።

በተለይም የመረዳዳትና የመደጋገፍ ወር በሆነው በዚህ ወር አቅመ ደካሞችን የማሰብና የመረዳዳት ባሕልም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም የምክር ቤቱ ምርጫ በሠላም እንደተጠናቀቀው ሁሉ፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ሕዝበ ሙስሊሙ የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሚካኤል ኅሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review