ለምርጫው ስኬታማነት የምሁራን ሚና

You are currently viewing ለምርጫው ስኬታማነት የምሁራን ሚና

ዛሬ ዓለም የምትሽከረከርባቸው ዋነኛ የሐሳብ ምህዋሮች በማመንጨት ምሁራን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ በምጣኔ ሀብት፣ በሳይንስ፣ በዴሞክራሲ፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች መስኮች ሐሳብ በማመንጨት አሻራቸውን አሳርፈዋል። አለማየሁ አረዳ (ዶ/ር) “ምሁሩ” በተሰኘው መጽሐፋቸው እንደገለጹት፤ ምሁራን በኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ መስክ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችሉ የመፍትሔ ሐሳቦችን በማመንጨትና ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደት ምሁራን በመደማመጥ፣ በመከባበር፣ በመደራደርና በመተጋገዝ የጋራ ሀገራዊ ተልእኮ መቅረፅ፣ ህብረተሰቡ የራሱን ዕድል በራሱ ተሳትፎ እንዲወስን በመፍትሔ ሐሳቦች በማስታጠቅ መምራት ይኖርባቸዋል፡፡

ከዴሞክራሲ ሥርዓት መገለጫዎች መካከል ምርጫ አንዱ ነው፡፡ ምርጫ ዜጎች ይመራኛል፣ ሀገርን ወደ ተሻለ የዕድገት ደረጃ ያሸጋግራል ብለው የሚያምኑበትን አካል የሚመርጡበትና ኃላፊነት የሚሰጡበት ሥርዓት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማካሄድ ሽር ጉድ እያለች ትገኛለች፡፡ መራጮች የመራጭነት ካርድ እያወጡ ይገኛሉ፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተለያዩ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የምርጫ ክርክሮችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የምርጫው ሂደት ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምርጫ ቦርድ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራት፣ መገናኛ ብዙኃን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝነት አለው፡፡ ምሁራንም እንደ አንድ የማህበረሰብ ክፍል በምርጫው ውጤታማነት ላይ የሚጫወቱት ሚና ይኖራል፡፡

የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር መኮንን አለኸኝ (ዶ/ር) ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት፤ የዴሞክራሲ አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ ውጤታማና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄድ ማለት ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር መተግበር ማለት ነው፡፡ ጠብን፣ ጥላቻንና ደም መፋሰስን በማስቀረት የሥልጣን ሽግግር በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የሚያስችል መሣሪያ ነው፡፡

ከዚህ አኳያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና ተአማኒነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምሁራን አይተኬ ሚና እንዳላቸው ዶ/ር መኮንን ያነሳሉ፡፡ በእርግጥ ምሁራኑ በየሀገራቱ እንዳለው የፖለቲካ ነጻነትና የዴሞክራሲ ዕድገት ደረጃ፣ የፖለቲካ መድረኩ መስፋትና መጥበብ ሚናቸው የሚወሰን ቢሆንም፤ በየትኛውም ሀገር በሀገር ልማት፣ ዴሞክራሲና ሰላም ግንባታ ቁልፍ ሚና አላቸው፡፡

ምርጫ የመንግሥት ሥልጣን ምንጭ ህዝብ መሆኑ የሚረጋገጥበት ነው፡፡ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ምሁራን በቅድመ-ምርጫ፣ በምርጫና በድኅረ-ምርጫ ወቅት ወሳኝ ሚናዎችን መጫወት እንደሚችሉና እንደሚጠበቅባቸው መኮንን(ዶ/ር) ያነሳሉ፡፡ በቅድመ ምርጫ ወቅት ዜጎች መምረጥና መመረጥ፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ መወሰን እንዲችሉና ሰላማዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለመራጮች የዜግነት ትምህርት በመስጠት ይሳተፋሉ።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ፕሮግራሞችና የፖሊሲ ሐሳቦችን በጥልቀት በመተንተንና ለህዝቡ በማሳወቅ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎችና በጥናትና ምርምር ተቋማት የሚሰሩ ምሁራን በማስረጃ ላይ በመንተራስ የህዝብ ውይይትን በማበረታታት፣ የፖሊሲ ሪፖርቶችና ምርጫው በሰላምና ደህንነት እንዲሁም በኢኮኖሚ ረገድ የሚኖረውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናቶችን በማካሄድና ውጤቶችን በማቅረብ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ በስነ-ዜጋ እና ስነ-ምግባር ጥናት ትምህርት ክፍል ውስጥ  መምህርና ተመራማሪ ታሪኩ ተስፋዬ ለዝግጅት ክፍላችን  እንደገለጹት፤ ምሁራን በማህበረሰብ ውስጥ ለሀገር የሚጠቅሙ አዳዲስ ሐሳቦችንና ዕውቀቶችን የማፍለቅና የማመንጨት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምሁራን በተለያዩ ፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫና በድኅረ ምርጫ ወቅት መከናወን ያለባቸው ሥራዎችን በተመለከተ በመረጃና በማስረጃ የተመሰረተ፣ ሳይንሳዊ አስተያየትና ትንታኔ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ምሁራን በምርጫው ሂደት የሚሳተፉ አካላት እውነታን በመያዝ መንቀሳቀስ እንዳለባቸው የማስተማር ኃላፊነት እንዳለባቸው መኮንን (ዶ/ር) ያስረዳሉ። የምርጫውን ሂደት ፍትሐዊነት መከታተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምርጫው ምን ያህል ፍትሐዊ እንደሆነ፣ ፍትሐዊ እንዲሆን ምን መሰራት እንዳለበት፣ ከማን ምን እንደሚጠበቅ በማስገንዘብ ረገድ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ለምርጫ ተቋማት ሙያዊ ምክር በመስጠት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ተቋማቱ የሚመሩበት ደንብና አሰራር ያላቸው ቢሆንም የህዝብን ጥቅምና ፍላጎት ማዕከል አድርገው እንዲንቀሳቀሱ ተገቢውን ምክር በመስጠት ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ምሁራን በቅድመ ምርጫ ወቅት የምርጫ ተቋማት (ብሔራዊ ምርጫ ቦርድና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት) ምርጫውን ለማካሄድ ያላቸውን ዝግጅት መተንተን፣ ክፍተቶች ካሉም እንዲስተካከሉ በመጠቆም ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ሊኖሩ የሚችሉ ብዥታዎችን፣ ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ ነገሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በማጥናት ሕዝቡ በሰከነ መንገድ በምርጫው እንዲሳተፍ በማድረግ ረገድም ያላቸው አበርክቶ ቀላል እንዳልሆነ የስነ ዜጋ እና ስነ-ምግባር መምህሩ ታሪኩ ያስረዳሉ፡፡

ምሁራን ዜጎች የዜግነት መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ የማስተማር ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ከመብትና ግዴታ ጋር የተያያዙ እንደ መቻቻል፣ አብሮነት፣ መከባበርና ልዩነትን ማክበር ባሉ የዴሞክራሲ እሴቶች ዙሪያ ዜጎችን በማሳወቅ ረገድ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚኖርባቸውም ያክላሉ፡፡

በምርጫው ወቅት ደግሞ ምሁራን ገለልተኛ ታዛቢ በመሆን መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለታዛቢነት ባይወከሉ እንኳን በራሳቸው እንደ ነጻና ገለልተኛ ታዛቢ ሆነው የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን፣ የምርጫውን ፍትሐዊነትና የሚፈጠሩ ችግሮች የሚፈቱበትን መንገድ ላይ መስራት እንደሚችሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መኮንን (ዶ/ር) ያስረዳሉ፡፡

ሌላው በምርጫው ወቅት ሊያጋጥም የሚችለውን ሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግርን በመከላከል ረገድ ምሁራን ሚና አላቸው፡፡ በመገናኛ ብዙኃን በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎችንና የጥላቻ ንግግሮችን በማጥራት፣ በመቃወምና በማጋለጥ ኃላፊነት የተሞላበት የፖለቲካ ውይይት እንዲፈጠር የድርሻቸውን መወጣት እንደሚችሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መኮንን (ዶ/ር) ያነሳሉ፡፡

ምሁራን ሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎን ማበረታታት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እርስ በእርሳቸው፣ ከገዥው ፓርቲ ጋር ሲወያዩ፣ በመገናኛ ብዙኃን ሲቀርቡ፣ የምርጫ ዘመቻ ሲያካሂዱ ሰላማዊ ፖለቲካን በሚያበረታታ መልኩ መሆን አለበት፡፡ የፖለቲካ ልዩነትን ማቻቻልና መቀበልን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ መራጩ ህዝብ እንዲላመድ በማድረግ ረገድ ደግሞ ምሁራን ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ 

የስነ- ዜጋና የስነ- ምግባር መምህሩ ታሪኩም ይህንን ሀሳብ ያጠናክራሉ፡፡ ምሁራን ኅብረተሰቡ በሰላማዊ ውይይት እንዲሳተፍ፣ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት መርሆችንና እሴቶችን እንዲገነዘብና እንዲተገብር፣ የህግ የበላይነት እንዲከበር በማሳወቅ በዴሞክራሲ ግንባታ ውስጥ ትልቅ ሚና መጫወት ይችላሉ፡፡ በምርጫ ሂደቶች ውስጥ የፖለቲካ ውጥረቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከዚህ አኳያ ምሁራን ግጭትን የሚያስቀር፣ የሰላም ባህልና የኅብረተሰቡን አንድነትን የሚያጠናክሩ ሀሳቦችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ህግን ለማክበር፣ የዴሞክራሲ መርሆችን ለመጠበቅና ዴሞክራሲያዊ ተሳትፎን ለማበረታታት የሚያግዙ ሐሳቦችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህም ምርጫው ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ነጻ እንዲሆን ያግዛል፡፡

በድኅረ-ምርጫ ወቅት ምሁራን የምርጫውን ውጤት በማስረጃ ላይ በመተንተን ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በምርጫው በትክክል የመራጩ ተሳትፎ ምን ይመስል ነበር? የምርጫ ሂደቱ ምን ጥንካሬና ድክመት ነበረው? ለወደፊቱ የሚጠቅሙ የተገኙ ትምህርቶችን በተመለከተ በሚገባ በመተንተን ለሕዝብና ለፖሊሲ አውጪዎች ምክረ ሐሳብ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የስነ- ዜጋ እና ስነ- ምግባር መምህሩ ታሪኩ እንደሚናገሩት፣ በድኅረ ምርጫ ወቅት ምሁራን የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አባሎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው፣ ሕዝቡ የምርጫ ውጤትን በሰላማዊ መንገድ እንዲቀበል የማስገንዘብ ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሀገራቸው ጉዳይ የሚመለከታቸውና በምርጫው ሂደትም መከናወን ቢኖርበት ብለው የሚያምኑት የራሳቸው የሆነ ጥቅምና ፍላጎትም ይኖራቸዋል፡፡ ነገር ግን ይላሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መኮንን (ዶ/ር)፣ በምርጫው የራሳቸውን ሳይሆን ሀገራዊ ፍላጎትና አጀንዳን ማበረታታት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ምሁራን ያለ ወገንተኝነት፣ በገለልተኝነትና በኃላፊነት ሀሳባቸውን ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው የሚያነሱት የስነ ዜጋ እና ስነ- ምግባር መምህሩ ታሪኩ፣ ይህ የእውቀት ነጻነታቸው የተጠበቀ እንዲሆንና ኅብረተሰቡም ሐሳባቸውን እንዲገዛና ያላቸው ተአማኒ ወይም አምስት ሊሆን ይችላል፤ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች በወጣቶች አማካኝነት ይታደላል። ባለፈው ዓመት በነበረው የኢድ በዓል እስከ 20 ኩንታል ዱቄት ተሰባስቦ ድጋፍ ፈላጊ ለሆኑ ዜጎች እንዲሰራጭ በማድረግ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ተደርጓል፡፡ በዘንድሮ በዓልም ይህ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በኢድ አልጥር በዓል የሚደረገው የመደጋገፍ እሴት በእለት ተለት ህይወት ሊተገበር እንደሚገባ ሼህ አሊ ይናገራሉ። “ዘካ መስጠት ግዴታ ነው፡፡ የሰዎችን ማህበራዊ ችግር ያቃልላል፡፡ የነብዩ መሐመድ  መርህንም መከተል ነው፡፡ የእርሳቸው መርህ አንዱ ለአንዱ ማዘን ነው፡፡ ለሰው የማያዝን  ከእኔ አይደለም፤ አላህ አያዝንለትም” ብለዋል፡፡ ይህንንም ህዝበ ሙስሊሙ እንዲተገብረው ማታ ከሶላት በፊት በየመስጂዱ ትምህርት ይሰጣል፡፡

አቅም የሚያንሳቸው፣ በችግር ምክንያት ደስታ የራቀቸው ሰዎች፣ ራሳችን ደስታ እንዳገኘን ሌሎችም ደስ እንዲላቸው ትንሽና ትልቅ ሳይል የዘካ ግዴታውን መወጣት ይኖርብናል፡፡ ነብዩ መሐመድ ‘በአንተ ቤት ደስታ ኖሮ በጎረቤትህ ከሌለ፤ በቤትህ እየበላህ፤ ጎረቤትህ የሚራብ ከሆነ አንተ ከእኔ አይደለህም፤ ነገ በአላህ ዘንድ ያስቀጣል” እንዳሉት በተግባር መገለጥ እንዳለበት ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

በጥቅሉ ዘካ ከራስ በፊት ለሌላው ማሰብን የሚያስተምር ሥርዓት ነው። እንዲህ ዓይነት እሴቶች አካል ጉዳተኞችን፣ ድኾችን፣ ዐቅመ ደካሞችን፣ አረጋውያንን፣ ሕጻናትንና የተለያዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ማህበራዊ ችግሮች በማቃለል ትስስርን፣ መደጋገፍንና መተባበርን የሚያጠናክር በመሆኑ ትውልዱን በማስተማር አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፡፡

 ነት እንዲጎለብት ያግዛል፡፡ የሚያቀርቡት ሐሳብም ለሀገር ሰላም፣ ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና ለህገ መንግስታዊ ስርዓት መጠናከር የሚያግዝ መሆን ይገባዋል፡፡ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት እሴቶችን፣ የህግ የበላይነትን፣ መራጮች መብትና ኃላፊነታቸውን እንዲያውቁ፣ ሰላማዊ የፖለቲካ ተሳትፎ እንዲኖር መስራት ይኖርባቸዋል። ይህም በሀገራችን የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲጠናከር ያደርጋል። የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ልማዶችም በህዝብ ዘንድ ግንዛቤና ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡

“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በአንድ ጀምበር የሚገነባ አይደለም፤ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ቀርቶ ጠንካራ ተቋማት የገነቡና የዳበረ ዴሞክራሲ አላቸው በሚባሉ ሀገራት ሳይቀር ምንም ዓይነት እንከን የሌለበት ምርጫ ማካሄድ ያስቸግራል” የሚሉት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መኮንን (ዶ/ር)፤ ምርጫ ሂደት እንደመሆኑ ከዓመት ወደ ዓመት እየተሻሻለ እንዲሄድ መስራትና ይህንንም ለህዝብ ማስገንዘብ ከምሁራን ይጠበቃል።

ምሁራኑ በምርጫው ሂደት የሚኖራቸውን ሚና ለመወጣት በፖለቲካው ውስጥ የሚታዩ ተግዳሮቶችን መጋፈጥ እንደሚጠበቅባቸው መኮንን (ዶ/ር) ያነሳሉ፡፡ ለምሳሌ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋልታ ረገጥ ወይም ጽንፍና ጽንፍ የሆነ አቋም  ሲያራምዱ ይታያል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለያየ ርዕዮተ ዓለምና ፕሮግራም ቢኖራቸውም የመጨረሻ ግባቸው ሀገርን የሚያሻግር ሀሳብ ማቅረብ ላይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ አንጻር ጽንፍና ጽንፍ የቆመ ሀሳብ ያላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲቀራረቡና ወደ መሀከል እንዲመጡ በማለዘብ ረገድ ምሁራን ሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ገዥው ፓርቲ ወይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ‘እንዲህ ናቸው፤ እድል አይሰጡም’ በማለት ራስህን ማግለል ሳይሆን ችግርም ካለ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

በዘርና ማንነት በመታጠር፤ ለራሳቸው ጎሳና ማንነት ወይም አካባቢ ብቻ በማድላት መስራት የለባቸውም፡፡ ሀገራዊ እይታን ማዕከል አድርገው መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለሀገር ግንባታ፣ ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር፣ የተሳካ ምርጫ ለማካሄድ የሚጠቅም ሐሳብ እስካላቸው ድረስ ሐሳባቸውን በመገናኛ ብዙሃን ለማካፈል ወደኋላ ማለት የለባቸውም፤ ገፍተው በመሄድ መሳተፍ እንዳለባቸውም የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ መኮንን (ዶ/ር) ያስገነዝባሉ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ አምስት ኪሎ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዮሐንስ አሰፋ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድ ቀድመው በማውጣት፤ የፖለቲካ ፓርቲ የክርክር መድረኮችን በመከታተል ይሆነኛል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተፈለገ ሁሉም ዜጋ የምርጫን ዓላማ በደንብ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡

በምርጫው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገር ይጠቅማል የሚሉትን ሐሳብ ይዘው ይቀርባሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ በትክክል ኅብረተሰቡን ሊጠቅም የሚችለው ሀሳብ የትኛው ነው የሚለውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ላይ ምሁራን ኅብረተሰቡን ማስተማር መቻል አለባቸው፡፡

ከምርጫው ሂደት አንስቶ የሚከናወኑ ሥራዎችን በመከታተልና ክፍተቶች ሲመለከቱም እንዲስተካከሉ በማድረግ መሳተፍ ይኖርባቸዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ከምንም በላይ በሰላማዊ መንገድ፣ በሐሳብ የበላይነት ችግሮችን መፍታት እንደሚቻልና ለዚህም በመምረጥ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማስተማር እንደሚጠበቅባቸው ይናገራሉ፡፡

በመጪው አምስት ዓመታት ይመራኛል ብሎ ለሚያምነው የፖለቲካ ፓርቲ ውክልና ለመስጠት የመራጭነት ካርድ በማውጣት የድምፅ መስጫ ዕለቱን እየተጠባበቀ እንደሚገኝ የሚናገረው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ነዋሪው ወጣት አክመል አህመድ፣ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲካሄድ ምሁራን ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው ይላል፡፡ ምሁራን የተሻለ እውቀትና ሐሳብ ያላቸው እንደመሆኑ ለከተማና ለሀገር ይበጃል ተብሎ የሚታሰበውን አካል ኅብረተሰቡ ለይቶ እንዲመርጥ በማንቃት፣ አቅጣጫ በማሳየትና በማስተማር  መሥራት እንደሚገባቸው ተናግሯል፡፡

በስንታየሁ ምትኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review