AMN- መጋቢት 22/2018 ዓ.ም
በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ሳኦቶሜን የገጠመችው ኢትዮጵያ በድምር ውጤት 4ለ0 በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ተቀላቅላለች።
በሞሮኮ የተደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ 3ለ0 ያሸነፉት ዋልያዎቹ በድሬዳዋ ስታዲየም የተከናወነውን የመልስ ጨዋታ 1ለ0 መርታት ችላለች።
ከአምስት ዓመታት በኋላ በሀገሩ ለተጫወተው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቸርነት ጉግሳ ብቸኛውን ግብ አስቆጥሯል።
በዛሬ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ይበልጥ ጨዋታ መቆጣጠር ላይ ማተኮሩ ተጨማሪ ግብ እንዳያስቆጥር አድርጎታል።
ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ ጨዋታ 3ለ0 ማሸነፉ እና ረጅም ጉዞ ማድረጉ በጨዋታ ቁጥጥር ላይ እንዲጠመድ ያደረገው ይመስላል።
ዋልያዎቹ በቀጣይ በኬንያ ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ አዘጋጅነት ለሚደረገው የ2027ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የምድብ ማጣሪያ የሚያደርጉ ይሆናል።
በሸዋንግዛው ግርማ