በበአላት ወቅት ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር ማሳለፍ ማህበራዊ ትስስርን እና አብሮነትን ያጠናክራል – አቶ ሞገስ ባልቻ

You are currently viewing በበአላት ወቅት ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር ማሳለፍ ማህበራዊ ትስስርን እና አብሮነትን ያጠናክራል – አቶ ሞገስ ባልቻ

AMN- ሚያዝያ 04/2018 ዓ.ም

በበአላት ወቅት ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር ማሳለፍ ማህበራዊ ትስስርን የሚያልቅና አብሮነትን የሚያጠናክር በጎ ተግባር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ገለጹ።

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በ14ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል 300 መቶ ለሚሆኑ አቅመ ደካማ አረጋውያን ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር ተካሂዷል ።

በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ማዕድ ያጋሩት የአዲስ አበባ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በበአላት ወቅት ከአቅመ ደካማ ወገኖች ጋር ማሳለፍ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጎለብት እና አብሮነትን የሚያጠናክር በጎ ተግባር ነዉ፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 27 የሚሆኑ የምገባ ማእከላት የተገነቡ ሲሆን በየማእከላቱም በየቀኑ ከ40ሺ በላይ አቅመ ደካማ ነዋሪዎችን መመገብ እንደተቻለ አቶ ሞገስ ገልጸዋል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ሀይሌ በበኩላቸዉ የከተማ አስተዳደሩ የአብሮነት እና የመረዳዳት እሴቶችን ለማሳደግ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

ነዋሪዎችም ለተደረገላቸዉ ድጋፍ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በአሉን ተደስተዉ ማሳለፋቸዉን ገልጸዋል፡፡

ማእድ ማጋራቱን የአዲስ አበባ ከተማ ምገባ ኤጀንሲ፣ የየካ ክፍለከተማ እና የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ መረጃ ኤጀንሲ በጋራ እንዳዘጋጁት ተመላክቷል።

በመሀመድኑር ዓሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review