AMN – ሚያዝያ 11/2018 ዓ.ም
በከተማችን አዲስ አበባ የገነባናቸው ዘመናዊ የስፖርት መሠረተ ልማቶች ውጤቱ አገራችን በአትሌቲክስ ዘርፍ ያላትን ታላቅ ዝና ዳግም ለማረገገጥ እድል ይሰጣል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
ከንቲባ አዳነች የተገነቡት የስፓርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ስፖርታዊ ኩነቶች፣ ከተማችን ማንኛውንም ዓይነት ዓለም አቀፍ ውድድር የማስተናገድ ብቃትና ደረጃ ላይ መድረሷን የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።
በመዲናችን የሚከናወኑ ውድድሮች ተተኪ አትሌቶችን ከማነቃቃታቸውም በላይ ለስፖርታዊ ቱሪዝም ዕድገት የጎላ ፋይዳ አላቸው።
ከተማችን ለነዋሪዎቿ ምቹ ፤ሳቢ ከማድረግ ባለፈ፣ ለዓለም አቀፍ ኩነቶች የስበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን በተግባር ያሳየ እውነታ ነው ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባ አዳነች ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ መድረኮችን ማዘጋጀት ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
አትሌቶቹም ሆነ እንግዶቹ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ውበት ይበልጥ እንደሚገነዘቡ ተስፋ አለኝ ሲሉ መግለፃቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።